ኮሌጁ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አርብቶ አደርና ቆላማ አካባቢዎች ቢሮ የቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት ጋር በመተባበር ስራ ዕድል ፈጠራ ላይ ያተኮረ ስልጠና እየሰጠ ነው።
የኮሌጁ ዲን አቶ አንዱዓለም ገብረመድህን በመክፈቻ ንግግራቸው፤ የወጣቶችን ስራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ ውጤታማ ለማድረግ የተቋማት ቅንጅታዊ አሰራር ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።
ኮሌጁ ከሌሎች ተቋማት ጋር በመቀናጀት በተለያዩ ዘርፎች ለበርካታ ዜጎች ለስራ ፈጠራ አጋዥ የሚሆኑ ስልጠናዎችን እየሰጠ ነው ብለዋል።
ኮሌጁ በርካታ የስልጠና አማራጮች ያሉት በመሆኑ ዜጎች ወደ ኮሌጁ በመምጣት የዕድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል።
ከማሰልጠን ባሻገር ለወጣቱ ስራ ዕድል መፍጠር የኮሌጁ የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ የኮሌጁ ምክትል ዲን ወይዘሮ ለጢፋ አህመድ ናቸው።
እየተሰጠ ያለው ስልጠና በስራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ የሚታዩ ክፍተቶችን በመሙላት ዘላቂ የሆነ የወጣቶች ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ፋይዳው የጎላ ነው ብለዋል።
ስልጠናው ለተከታታይ 21 ቀናት የሚሰጥ መሆኑን ተናግረው፤ ሰልጣኞች በአግባቡ ተከታትለው ተጠቃሚ እንዲሆኑ አሳስበዋል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አርብቶ አደርና ቆላማ አካባቢዎች ቢሮ የቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት አስተባባሪ አሸብር ቆጭቶ(ዶ/ር)፤ ስልጠናው ወጣቶችን ከስራ ጋር ለማስተሳሰር ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን አመላክተዋል።
ከካፋና ከምዕራብ ኦሞ ዞኖች ቆላማ አካባቢዎች የተውጣጡ በማህበር የተደራጁ ወጣቶች በዳቦ መጋገሪያና በእንጨት ስራዎች ዙሪያ ስልጠና መጀመራቸውን ገልጸዋል።
ሰልጣኞች በተደራጁበት ስራ የጽንሰ ሀሳብ ስልጠና ከተሰጣቸው በኋላ የተግባር ልምምድ እንደሚያደርጉ አመላክተዋል።
ዘጋቢ፡ ሀብታሙ ኃይሌ – ከቦንጋ ጣቢያችን
የወጣቶችን ስራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ ውጤታማ ለማድረግ የተቋማት ቅንጅታዊ አሰራር ወሳኝ መሆኑን የቦንጋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ገለጸ

More Stories
ህዝበ ክርስቲያኑ የ2019 ዓ.ም የእንቁጣጣሽ በዓልን በሚያከብርበት ወቅት አቅመ ደካሞችን በመደገፍ ሊሆን እንደሚገባ የጠምባሮ ልዩ ወረዳ የሀይማኖት አባቶች ተናገሩ
የ2018 በጀት ዓመት ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ታላላቅ ስኬቶችን ያስመዘገበችበት እና የዲጂታል ሽግግር የሉዓላዊነቷ ምሰሶ መሆን የቻለችበት አመት መሆኑን አቶ አልማው ዘውዴ ገለፁ
ጳጕሜን 5 “የነገው ቀን” በኮሬ ዞን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው