በጌዴኦ ዞን ሥራና ክህሎት መምሪያ የ2018 ዓ ም የ6 ወራት አፈፃፀም ግምገማና የቀጣይ ወራት ትኩረት አቅጣጫ ዙሪያ የንቅናቄ መድረክ በዲላ ከተማ ተካሄደ
መድረኩን በንግግር የከፈቱት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጌዴኦ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ እና የመንግሥት ዋና ተጠሪ ተመስገን ጥላሁን፥ የተፈለገውን ምርትና ምርታማነት በማሳደግ የብልፅግናን ጉዞ እውን ለማድረግ ከሰው ሀይል ባሻገር በክህሎትና ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጂ መጠቀም ለነገ የሚባል ጉዳይ አይደለም ብለዋል።
የጌዴኦ ዞን ሥራና ክህሎት መምሪያ ኃላፊ አቶ ታደለ ጥላሁን በበኩላቸው፥ የትኛውም ተግባር ክህሎት መር እንዲሆን ስለሚጠበቅ እያንዳንዱ መዋቅር በሙሉ በባለቤትነት መሥራት እንደሚጠበቅበት አስረድተዋል።
ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂ መጠቀም ይጠበቃል ያሉት አቶ ታደለ፥ ዜጎች ከሥልጠና ባሻገር በተሳተፉበት ዘርፍ ሁሉ ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ማድረግ ያስፈልገናል ብለዋል።
የዞኑ ሥራና ክህሎት መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ አክሊሉ በደቻ፥ መምሪያው የረጅምና አጭር ጊዜ ዕቅድ በማዘጋጀት የተቋም ግንባታ፣ የክህሎት ልማት፣ የሥራ ዕድል ፈጠራና የኢንዱስትሪ ሠላም ማስፈን ተግባራትን በትኩረት መስኮች ለመወጣት የሚያስችሉ በየደረጃ የሚተገበሩ ስትራቴጂ ግቦችና የሪፎርም ሀሳቦችን በማስቀመጥ ወደ ውጤት ለማሸጋገር እየተሠራ እንደሚገኝ ነው የገለፁት።
በመቀጠልም የ2018 ዓ/ም የ6 ወራት ክንውን ሪፖርትና የቀጣይ ወራት የትኩረት አቅጣጫ ዕቅድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
የተሻለ አፈፃጸም ያስመዘገቡ መዋቅሮች፣ ሥራ አጥንና ሥራን ለማገናኘት ግንዛቤ መፍጠርና ሀብት የማፈላለግ ተግባር ቅድሚያ በመስጠት ጥሩ እንቅስቃሴ እያደረጉ እንደሚገኙ አስረድተዋል።
አስተያየት ከሰጡት ተሳታፊ አመራሮችና ባለሙያዎች አቶ አሸናፊ ህርቤ፣ አቶ ተካልኝ በቀለና ሌሎችም ጠንካራ አፈፃፀምን ማስቀጠልና በጉድለት የታዩትን በቀጣይ ወራት በትጋት በመሥራትና ማረም እንደሚጠበቅ አመላክተው፥ የፊት አመራሮችም ድጋፍና ክትትል እንዲያደርጉ ተናግረዋል።
ዘጋቢ፡ ምርጫ መላኩ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
በጌዴኦ ዞን ሥራና ክህሎት መምሪያ የ2018 ዓ ም የ6 ወራት አፈፃፀም ግምገማና የቀጣይ ወራት ትኩረት አቅጣጫ ዙሪያ የንቅናቄ መድረክ በዲላ ከተማ ተካሄደ

More Stories
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ 25 ሺህ 338 ሊትር ቤንዝልና 62 ሺ 686 ሊትር ናፍጣ በቁጥጥር ስር መዋሉን የክልሉ ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ አስታወቀ
ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ፍትሐዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የፍትህና የጸጥታ ዘርፍ አመራሮችና ባለሙያዎች ሚና የላቀ መሆኑ ተገለጸ
ከአየር ንብረት ተፅዕኖ ጋር እየተስተዋሉ ያሉትን ችግሮች ለመከላከል ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አካባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣን አስታወቀ