በዞኑ በዘንድሮ በልግ እርሻ ከ1መቶ 29 ሺህ በላይ ሄክታር ማሳ በተለያየ አዝርዕት ለመሸፈን መቻሉም ተጠቁሟል።
በዞኑ አንዳንድ አከባቢዎች የበልግ ምርቶች እየደረሱ መሆኑ አርሶ አደሮች ከቤት ፍጆታቸው ባለፈ ለአከባቢው ገበያና ማዕከላዊ ገበያ ምርቶቻቸው እያቀረበ መሆኑን ከዞኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
በልግ እርሻ ምርት ቶሎ ከሚደርስባቸው አከባቢዎች መካከል ዳሞት ፑላሳ ወረዳ አንዱ ነወ።
በወረዳው በልግ እርሻ ከተሸፈነው የተሻለ ምርት እናገኛለን ሲሉ ያነጋገርናቸው አርሶ አደሮች ተናግረዋል።
ዘመናዊ የአስተራረስ ዘዴ በመከተል እንድሁም የተለያየ ቴክኖሎጂ በመጠቀም ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ የባለ ድርሻ አካላት ድጋፍ ለውጤታማነቱ እንዳገዛቸው አርሶ አደሮች ተናግረዋል።
በዘንድሮ በልግ እርሻ ከባለፈው ዓመት የተሻለ ምርት ለማግኘት ከማሳ ዝግጅት ጀምሮ አርሶ አደሩ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ሙሉ የግብርና ግብዓት ተጠቅሞ ማሳቸውን በተለያየ አዝርዕት ሽፋን እንዲያገኝ መደረጉን የወላይታ ዞን ግብርና መምሪያ ምክትል ኃላፊና እርሻ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ከሲሳይ ሳሙኤል ገልጸዋል።
የአርሶ አደሮችን ምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ከመቸውም ጊዜ በላይ በተሻለ ሁኔታ በተደረገላቸው ድጋፍና ክትትል በልግ እርሻ የተሻለ ምርት ይጠበቃል ሲሉ አቶ ሲሳይ አብራርተዋል ።
አዘጋጅ ፡ ተስፋሁን ሳርካ፡ከዋካ ቅርንጫፍ

More Stories
የጌዴኦ ዞን ምክር ቤት 32ኛ የምክር ቤቶች የጋራ ምክክር ፎረም አካሄደ
ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ደቡብ ሱዳንን አስጠነቀቀ
የጌዴኦ ዞን ምክር ቤት 32ኛ የምክር ቤቶች የጋራ ምክክር ፎረም እያካሄደ ነው