በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ሲካሄድ የቆየው የዞኑ ልዩ ልዩ ስፖርቶች ሻምፒዮናና 21ኛው የባህል ስፖርት ዉድድር ፍጻሜዉን አገኘ
በሻምፒዮናው በእግር ኳስ ለፍፃሜ በቀረቡት የቸሀ ወረዳና የወልቂጤ ከተማ እግርኳስ ቡድኖች መካከል የተደረገው ጨዋታ በመደበኛው ሰአት በአቻ ውጤት ቢጠናቀቅም በመለያ ምት የቸሃ ወረዳ አምስት ለአራት በሆነ ውጤት በማሸነፍ የዋንጫ ባለቤት ሆኗል።
ለደረጃ በተደረገ መርሃ ግብር የጉንችሬ ከተማና የእምድብር ከተማ አስተዳደር ባደረጉት ጨዋታ በተመሳሳይ በመለያ ምት እምድብር ከተማን አሸናፊ በማድረግ ሶሥተኛ ደረጃን ይዞ እንዲያጠናቅቅ አድርጎታል።
በሌሎች ዘርፎች በአትሌቲክስ የጌታ ፣ በቦሊቦል አበሽጌ ፣በባህል ስፖርት ሙህር አክሊል ፣በቴኳንዶ ጉመር ወረዳን ሻምፒዮን ሲያደርግ ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የፀባይ ዋንጫ ተሸለሚ ሆኗል።
በውድድሩ የመዝጊያ መርሀ ግብር የጉራጌ ዞንና የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር አመራር አካላት በክብር እንግድነት ታድመውበታል ።
በውድድሩ የተሻለ አፈፃፀም ላሳዮ ዳኞች ተጫዎቾች እንዲሁም አስተዋፅዖ ላበረከቱ ተቋማትና ግለሰቦች እውቅና በመስጠት ተጠናቋል።
ዘጋቢ፡ አማረ መንገሻ- ከወልቂጤ ቅርንጫፍ
More Stories
የ2017 የጋሞ ዞን ልዩ ልዩ ስፖርቶች ሻምፒዮና ውድድር በወንዶች እግር ኳስ ውድድር በዳራማሎ ወረዳ አሸናፊነት ተጠናቀቀ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የጅቡቲ አቻውን 6ለ1 አሸነፈ
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ የምስክር ወረቀት ተሰጠው