ብሔራዊ ምክክር ሀገራዊ አንድነትን ከማጠናከር ባሻገር ችግሮችን በውይይትና በሀሳብ የበላይነት ለመፍታት መሠረት እንደሚጥል ተገለጸ

ብሔራዊ ምክክር ሀገራዊ አንድነትን ከማጠናከር ባሻገር ችግሮችን በውይይትና በሀሳብ የበላይነት ለመፍታት መሠረት እንደሚጥል ተገለጸ

ሀዋሳ፡ ሐምሌ 09/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) ብሔራዊ ምክክር ሀገራዊ አንድነትን ከማጠናከር ባሻገር ችግሮችን በውይይትና በሀሳብ የበላይነት ለመፍታት መሠረት እንደሚጥል በሆሳዕና ከተማ ያነጋገርናቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ተናገሩ፡፡

የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ያሳተፈ ብሔራዊ ምክክሩ ዘላቂ ሀገራዊ ልማትንና ሠላምን ማረጋገጥ ያስችላል ተብሎ ይጠበቃልም ብለዋል።

ኢትዮጵያ ለሀገራዊ ችግሮቿ ሀገራዊ መፍትሔን ማበጀት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ የምክክር ኮሚሽን አቋቁማ እሄደች ያለችበት ሂደት የሚበረታታ ነው ሲሉ በሆሳዕና ከተማ አስተያየታቸውን የሰጡን የህብረተሰብ ክፍሎች ተናግረዋል።

ሠላም ለሁሉ ዐቀፍ ሀገራዊ ልማት መሠረት መሆኑን ጠቁመው፥ ኢትዮጵያ አሁን እያካሄደች የሚገኘውን የልማት ግስጋሴ የሚገቱ ማናቸውንም የሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ የሚስተዋሉ ችግሮችን በአንድነት መመከት እንዲቻል ምክክሩ ፋይዳው የጎላ መሆኑን አመላክተዋል።

የምክክር ሂደትን ያለፉ ሀገራት ችግሮቻቸውን በጠረጴዛ ዙሪያ በመፍታት በልማት ጎዳና እንደሚገኙ ጠቁመው፥ ውስጣዊ አንድነት ለሀገር ሁለንተናዊ ልማት ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል።

የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ያሳተፈ ብሔራዊ ምክክሩ ዘላቂ ሀገራዊ ልማትንና ሠላምን ማረጋገጥ ያስችላል ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል።

ሀገር በምክክር ትፀናለች ያሉት አስተያየት ሰጪዎቹ፥ ዘላቂ ልማቷንና ሠላሟን ማረጋገጥ በሚቻልባቸው ሂደቶች ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ዘጋቢ: አማኑኤል አጤቦ – ከሆሳዕና ጣቢያችን