በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ሲካሄድ የቆየው የዞኑ ልዩ ልዩ ስፖርቶች ሻምፒዮናና 21ኛው የባህል ስፖርት ዉድድር ፍጻሜዉን አገኘ

በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ሲካሄድ የቆየው የዞኑ ልዩ ልዩ ስፖርቶች ሻምፒዮናና 21ኛው የባህል ስፖርት ዉድድር ፍጻሜዉን አገኘ

በሻምፒዮናው በእግር ኳስ ለፍፃሜ በቀረቡት የቸሀ ወረዳና የወልቂጤ ከተማ እግር ኳስ ቡድኖች መካከል የተደረገው ጨዋታ በመደበኛው ሰአት በአቻ ውጤት ቢጠናቀቅም በመለያ ምት የቸሃ ወረዳ አምስት ለአራት በሆነ ውጤት በማሸነፍ የዋንጫ ባለቤት ሆኗል።

ለደረጃ በተደረገ መርሃ ግብር የጉንችሬ ከተማና የእምድብር ከተማ አስተዳደር ባደረጉት ጨዋታ በተመሳሳይ በመለያ ምት እምድብር ከተማን አሸናፊ በማድረግ ሶሥተኛ ደረጃን ይዞ እንዲያጠናቅቅ አድርጎታል።

በሌሎች ዘርፎች በአትሌቲክስ የጌታ፣ በቦሊቦል አበሽጌ፣ በባህል ስፖርት ሙህር አክሊል፣ በቴኳንዶ ጉመር ወረዳን ሻምፒዮን ሲያደርግ ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የፀባይ ዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።

በውድድሩ የመዝጊያ መርሀ ግብር የጉራጌ ዞንና የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር አመራር አካላት በክብር እንግድነት ታድመውበታል።

በውድድሩ የተሻለ አፈፃፀም ላሳዮ ዳኞች ተጫዋቾች እንዲሁም አስተዋፅዖ ላበረከቱ ተቋማትና ግለሰቦች እውቅና በመስጠት ተጠናቋል።

ዘጋቢ፡ በአማረ መንገሻ – ከወልቂጤ ጣቢያችን