በክልሉ 20 ሺህ 229 የታጠበና ያልታጠበ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ቀርቧል – ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ

በክልሉ 20 ሺህ 229 የታጠበና ያልታጠበ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ቀርቧል – ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ

ሀዋሳ፡ ጥር 30/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) በክልሉ 20 ሺህ 229 የታጠበና ያልታጠበ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ መቅረቡን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ ገለጹ፡፡

ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በክልል ምክር ቤት የአስፈፃሚ አካላት ሪፖርት እያቀረቡ ይገኛሉ።

የቡና ልማት ዘርፍን ለማሳደግ አበረታች ተግባራት ስለመከናወናቸው የገለፁት ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ፤ 71 ነጥብ 2 የችግኝ ቦታዎችም እንክብካቤ ስለመደረጉ ገልፀዋል።

ከክልሉ 22 ሺህ ቶን ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ ከታቀደው 20 ሺህ 229 የታጠበና ያልታጠበ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረብ ተችሏልም ብለዋል።

22 ሺህ ቶን በኮንትሮባንድ ሲዘዋወር የነበረ ቡና መያዝ መቻሉንም ገልፀዋል።

የቡና ልማት ተግባር ክልሉ በማምረት ከሚታወቅባቸው ቀዳሚ ምርቶች አንዱ መሆኑም ተመላክቷል።

ዘጋቢ፡ ዮሐንስ መካሻ – ከዋካ ጣቢያችን