በጎፋ ዞን የዑባ ደብረ ፀሐይ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከመደበኛ የአባላት ወርሃዊ መዋጮ በተጨማሪ 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር በላይ የዓይነትና የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል።
በርክብክብ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የጎፋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ቦረና ቦላዶ፤ ፓርቲው ከአባላትና ደጋፊዎች ከ89 ሚሊየን ብር በላይ ለመሰብሰብ አቅዶ እየተሰራ መሆኑን ተናግረው፤ በዑባ ደብረ ፀሐይ ወረዳ በአይነትና በገንዘብ 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር በላይ ከሁሉም ቀበሌያት የተሰበሰበውን ሀብት ተረክበዋል።
የፓርቲውን አቅም በፋይናንስ መደገፍ ጠንካራ ሀገረ መንግስት ለመፍጠር ወሳኝ በመሆኑ አባላትና ደጋፊዎች ከፓርቲው ጎን መሆን እንዳለባቸው አሳሰበው፤ ለወረዳው የፓርቲ አመራሮችና አባላት በዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስም ምስጋና አቅርበዋል።
የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊና የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ መልካሙ ሩንጎ በበኩላቸው፤ ንቅናቄው በ20 ቀበሌያት በከፍተኛ መነሳሳት መከናወኑን ተናግረው በዓይነት 930 ሺህ ብር የሚገመቱ ሰባት ሰንጋ በሬዎች እና 3 ቡሉኮዎች (ባህላዊ አልባሳት) በጥሬ ገንዘብ 255 ሺህ ብር በአጠቃላይ ከ 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ሀብት ተሰብሰቦ ማስረከባቸውን ተናግረዋል።
በቀጣይ እየተሰበሰበ ያለውን ተጨማሪ ሀብት በአጭር ጊዜ ለማሰረከብ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።
የዑባ ደብረ ፀሐይ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ደመቀች ዝና በበኩላቸው፤ አባላትና ደጋፊዎች ለፓርቲው በአይነትና በገንዘብ ያደረጉት ድጋፍና መነሳሳት የፓርቲውን ህዝባዊ መሰረት ይበልጥ የሚያጠናክር በመሆኑ የሴቶች አባላትና ደጋፊዎች ለፓርቲው አሰፈላጊውን ድጋፍ እያደረጉ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ዘጋቢ፡ ስንታየሁ ሙላቱ – ከሰውላ ጣቢያችን

More Stories
የግል እና የጋራ መጸዳጃ ቤቶችን በተገቢው በመጠቀም ተላላፊ የሆኑ በሽታዎችን አስቀድሞ መከላከል እንደሚገባ በጉራጌ ዞን የእኖር ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት አስገነዘበ
12 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በተቋማት የድርጊት መርሐ-ግብርና በፀደቀላቸው በጀት መሠረት ማሰራጨቱን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ አስታወቀ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር) በምስራቅ ጉራጌ ዞን ቡኢ ከተማ አስተዳደር እየተገነባ የሚገኘውን ብሉ ኤለፋንት ፋይበር ቦርድ ካምፓኒ ጎበኙ