የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተደራሽነትን በማሳደግ በቴክኖሎጂ የበለፀገ ዜጋን ለማፍራት በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ ተጠቆመ
ሀዋሳ፡ ጥር 28/2016 ዓ.2016 (ደሬቴድ) የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተደራሽነትን በማሳደግ በቴክኖሎጂ የበለፀገ ዜጋን ለማፍራት በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አሳሰበ።
ቋሚ ኮሚቴው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮንና የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ቢሮን የ2016 የ6 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ገምግሟል።
ለማህበራዊ ችግር ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል በኢንዱስትሪዎች አከባቢ ለሰራተኞች ምቹ የስራ ቦታ ለመፍጠር ብሎም በህፃናት፣ በቤት ሰራተኞች ላይ የሚደረግ የመብት ጥሰትን ለመከላከል ሰፊ ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝ የክልሉ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በሪፓርቱ አመላክቷል።
የተአድሶ ማዕከል ለአካል ጉዳተኞች አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ አደረጃጀቱን የማጠናከር ስራ መከናወኑን የጠቆሙት የክልሉ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዋኖ ዋሎሌ ከረጂ ድርጅቶች ጋር በመተባበር የዘርፉን ተግዳሮት ለመፍታት እንደሚሰራ አብራርተዋል ።
በበጀት ዓመቱ የስራ ስምሪት አገልግሎት እንዲስፋፋ፣ የኢንዱስትሪ ሰላም እንዲሰፍን የሰራተኛው ደህንነትና ጤንነት እንዲጠበቅ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንዳለ የጠቆሙት ዶክተር ዋኔ የአካል ጉዳተኞችን፣ የአረጋዊያንን ኢኮኖሚና ማህበራዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰራ እንዳለም ገልፀዋል።
በተመሳሳይም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ቢሮ በሪፓርቱ እንደገለፀው ቴክኖሎጂን በማስፋፋት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ፣ የዲጂታል ቤተ-መጻሕፍት ማስፋፋት፣ የሙያ አግባብነትና ጥራትን በዘላቂነት ለመፍታት የተግባር ስልጠና ላይ ትኩረት መደረጉን ጠቁሟል።
የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተደራሽነትን በማሳደግ በቴክኖሎጂ የበለፀገ ዜጋን ለማፍራት በትኩረት መሰራቱን ተገልጿል።
በጀት በወቅቱ ያለመላቀቅ፣ የጥሬ ዕቃ ችግር የግንባታ ስራ መስተጓጐል እና መሰል ችግሮች ቢሮውን በ6 ወራት ውስጥ እንዳጋጠመው በመድረኩ ተገልጿል።
የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተደራሽነትን በማሳደግ በቴክኖሎጂ የበለፀገ ዜጋን ለማፍራት ትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ በምክር ቤቱ የማህበራዊ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ እመቤት ወንድሙ አሳስበዋል።
በማህበራዊ ዘርፍም የሴት አካል ጉዳተኞችን ችግር በመቅረፍ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ በቀጣይ ተጨባጭ ተግባራት መከናወን እንዳለባቸውም በመጠቆም።
በቀረቡት ሪፖርቶች ላይ አስተያየትና ሀሳብ ተሰንዝሮ ሰፊ ማብራሪያዎች ከሚመለከታቸው አካላት ተሰጥቷል።
ዘጋቢ ፡ ተመኙህ ገረሱ – ከአርባምንጭ ጣቢያችን
More Stories
የተሻሻሉ የእንስሳት ዝርያዎችን በማስፋፋት የእርባታ ስራውን ምርታማነት የማሳደግና የዘርፉን ተጠቃሚነት ለማጎልበት የሚያስችሉ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን የጂንካ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ
የጂንካ ዩኒቨርሲቲ አዲስ አፈር አልባ የመኖ አመራረት ዘዴን አስተዋወቀ
በርካቶችን ከድካም የሚታደግ የፈጠራ ውጤት