የዘመናት ጥያቄያቸው የነበረ የመብረት ዝርጋታ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት በመጀመሩ መደሰታቸውን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀዲያ ዞን ሌሞ ወረዳ ለሬባና ሮሜ ቀበሌ ነዋሪዎች ገለጹ

የዘመናት ጥያቄያቸው የነበረ የመብረት ዝርጋታ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት በመጀመሩ መደሰታቸውን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀዲያ ዞን ሌሞ ወረዳ ለሬባና ሮሜ ቀበሌ ነዋሪዎች ገለጹ

ለመብራት ዝርጋታ ከ8 ሚሊየን ብር በላይ በጀት ወጪ መደረጉም በወቅቱ ተገልጿል::

ድህነትን በማስወገድ ብልጽግናን ለማረጋጋጥ ህብረተሰቡ በግብርና ስራ ላይ ትኩረት ማድረግ እንደለበት የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም መጫ ተናግረዋል።

አንዳንድ የለሬባና ሮማ ቀበሌ ነዋሪዎች ከዚህ ቀደም በቀበሌያቸው መብራት ባለመኖሩ በተማሪዎች ጥናትና ውጤት አሉታዊ ተጽዕኖ እያሳደረ እንደነበረና ወፍጮ ቤት ባለመኖሩ ዕሩቅ መንገድ እንደሚጓዙ እና የዘመኑን ቴክኖሎጂ መጠቀም እንዳልቻሉ ገልጸዋል።

ችግሩን ለመቅረፍ በሀገርና ከሀገር ውጭ የሚገኙ ተወለጆች ተቀናጅተው በሰበሰቡት ገቢ የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት በማግኘታቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል።

በምረቃ ፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም መጫ ለሁሉም ነገር መሰረት ብርሃን መሆኑን ገልጸው በቀጣይም ቀሪ የመሰረተ ልማት ስራዎችን ለመከወን መትጋት መስራት ይገባል ብለዋል።

የአካባቢው ህዝብ ጥያቄ የሆኑት ቀሪ መሰረተ ልማቶች እንደሚመለሱ የተናገሩት አቶ አብርሃም ጤና ጣቢያና የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት እስከ 2016 መጨረሻ ድረስ ሙሉ በሙሉ በመንግስት እንደሚከናወኑ ቃል ገብተዋል።

የቀበሌ ነዋሪዎቹ ለልማት ያላቸው ተነሳሽነት ለሌሎች አካባቢዎችም ጥሩ ተሞክሮ እንደሚሆንም ገልጸዋል።

ድህነትን በማስወገድ ብልጽግናን ለማረጋጋጥ ህብረተሰቡ በግብርና ስራ ላይ ትኩረት ማድረግ እንደለበት ዋና አስተዳዳሪው አሳስበዋል።

የሌሞ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኢዮብ ጩፋሞ በበኩላቸዉ አዲሱ ማዕከላዊ ክልል በአዲስ ምዕራፍ በአዲስ ዕቅድ ወደ ብልጽግና ጉዞ በተገባበት ማግስት መመረቁ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል።

ሀገሪቱ ካለችበት የኢኮኖሚ ጥገኝነት በማላቀቅ ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጂ በመጠቀም በጋራ ዕሳቤ በአንድነት እርብርብ ማድረግ ይጠበቃል ብለዋል።

የቀበሌው ህብረተሰብ፣ አመራር፣ ምሁራንና ባለሀብቶች የዘረጉትን የልማት ስራ በቀጣይ መንግስት የቀረውን የልማት ስራ ለማከናውን በሚያደርገው እንቅስቃሴን ለመደገፍ ጥረት ማድረግ እንደሚገባም አቶ ኢዮብ አሳስበዋል።

የመብራት ዝርጋታ ኮሚቴ ሰብሳቢ አባገደ ባሻ አቡቴ እንደገለጹት በውጭና ሀገር ውስጥ የሚገኙ የቀበሌ ተወላጆችን በማስተባበር በተገኘው ከ8 ሚሊየን በሚበልጥ ወጪ ከብዙ ልፋት በኋላ ተገንብቶ ለአገልግሎት በቅቷል ብለዋል።

ዘጋቢ፡ ሳሙኤል መንታሞ – ከሆሳዕና ጣቢያችን