በክልሉ ሰላምን ለማረጋገጥ በተደረገው የተቀናጀ ርብርብ ካለፉት አመታት ወዲህ የተሻለ ውጤት መመዝገቡ ተገለጸ
ሀዋሳ፡ ጥቅምት 26/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) በክልሉ ሰላምን ለማረጋገጥ በተደረገው የተቀናጀ ርብርብ ካለፉት አመታት ወዲህ የተሻለ ውጤት መመዝገቡን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሠላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ አንድነት አሸናፊ ተናገሩ።
የክልሉ ሠላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከዞኑ ሰላም፤ ፀጥታና ሚሊሻ መምሪያና ከወረዳና ከተማ አስተዳደሮችን የ2015 አፈጻጸም ግምገማና የ2016 ዕቅድ ዙሪያ የውይይት መድረክ በቦንጋ ከተማ እያካሄደ ነው።
የቢሮው ኃላፊ አቶ አንድነት አሸናፊ በመክፈቻ ንግግራቸው በ2015 ዓ.ም በየደረጃው ባሉ መዋቅሮች የህዝቡን ሠላምና ጸጥታ ለማስጠበቅ በትኩረት ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል።
በዘርፉም የተቀናጀ ርብርብ በመደረጉ ካለፉት አመታት የተሻለ ውጤት የተመዘገበ ቢሆንም ከሚጠበቀው አንጻር አሁንም በትኩረት መስራትን እንደሚጠይቅ አቶ አንድነት አሸናፊ አመላክተዋል።
ኢትዮጵያ በተለያዩ ፈተናዎች ውስጥ ሆና ስኬቶችን ለማስመዝገብ የምትጥርበት ወቅት ላይ እንገኛለን ያሉት አቶ አንድነት ፈተናዎችን አልፋ ወደ ሁለንተናዊ ብልፅግና እንድትደርስ በጋራ መረባረብ እንደሚገባ ጠቁመው ያለ ሰላም ሁለንተናዊ ብልፅግናን ማረጋገጥ እንደማይቻልም ገልጸዋል።
በኢኮኖሚ፤ በማህበራዊና በፓለቲካ ዘርፎች ውጤት ማስመዝገብ የሚቻለው ሠላም ሲኖር ብቻ በመሆኑ ሁሉም ለሠላም ቅድምያ እንዲሰጥ አሳስበዋል።
የአፈጻጸም ግምገማ ተሳታፊዎችም ባለፉት ጊዜያት የተመዘገቡ ውጤቶችን አጠናክሮ ለማስቀጠልና ክፍተቶችን በማረም በቀጣዩ የሥራ ምዕራፍ የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ ልዩ ትኩረት እንደሚሻም የቢሮው ኃላፊው ተናግረዋል።
ዘጋቢ፡ ሀብታሙ ታደሰ – ከቦንጋ ጣቢያችን
More Stories
የቀቤና ልማት ማህበር (ቀልማ) የማህበረሰቡን ሁለትናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የያዛቸው ዋና ዋና ግቦች ለማሳካት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት መዘጋጀታቸውን አባላቱ ገለጹ
የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒቶች መላመድ ለሰው ልጆች ስጋት እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ
በሀዲያ ዞን ከ8መቶ 50ሺህ በላይ የተለያዩ የህብረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራት መከናወናቸው ተገለፀ