ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አዲስ የተቋቋመውን የኢትዮጵያ አካል ድጋፍ አገልግሎት ማዕከል መረቁ
የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከ3 ዓመት በፊት እንዲቋቋም አቅጣጫ ባስቀመጡት መሰረት አዲስ የተቋቋመውን የኢትዮጵያ አካል ድጋፍ አገልግሎት ማዕከል ዛሬ ረፋድ ላይ መመረቃቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
ማዕከሉ በተፈጥሮ እና በአደጋ ምክንያት የአካል ጉዳተኛ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች በሀገር ውስጥ አጋዥ ቁሶችን ለማምረት እና ለማቅረብ የተቋቋመ ማዕከል መሆኑ ተመላክቷል።
የኢትዮጵያ አካል ድጋፍ አገልግሎት ማዕከል አጋዥ ቴክኖሎጂዎችን ለማምረት፣ ለማደስ እና ለማቅረብ የተቋቋመ ሲሆን ተደራሽ፣ ጥራት ያለው እና ደንበኛ ተኮር የሰው ሰራሽ እና የአካል ድጋፎች አገልግሎቶችን ለህብረተሰቡ የሚሰጥ መሆኑም ተገልጿል።

More Stories
አቶ ይሁን አሰፋ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የየም ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሾሙ
አቶ መብራቴ ወልደማርያ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በመሆን ተሾሙ
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከተባባሪ አካላት ጋር በመሆን ያስገነባቸውን 100 መኖሪያ ቤቶችን ለኮንሶ ዞን ተፈናቃዮች በይፋ አስተላለፈ