ሉሲዎቹ ከሩዋንዳ ጋር የመልስ ጨዋታቸውን ዛሬ ያደርጋሉ
በ2028 ኦሎምፒክ የሴቶች እግርኳስ ሁለተኛ ዙር ማጣሪያ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከሩዋንዳ ጋር በድሬዳዋ ስታዲየም ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ ያደርጋል።
ሉሲዎቹ በመጀመሪያው ጨዋታ ኪጋሊ ላይ 1ለ0 አሸንፈው መመለሳቸው ይታወሳል።
በአሰልጣኝ ቻለው ለሜቻ በሚመራው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በኩል ግብ ጠባቂዋ ታሪኳ በርገና እና አጥቂዋ ንግስት በቀለ በጉዳት ምክንያት ከዛሬው ጨዋታ ውጪ ሲሆኑ በመጀመሪያው ጨዋታ በስብስቡ ያልተካተተችው አምበሏ ሎዛ አበራ ለዛሬው ጨዋታ ዝግጁ መሆኗ ተገልጿል።
በጨዋታው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አረንጓዴ ማልያ፣ቢጫ ቁምጣ እና ቀይ ካሶተኒ ለብሰው ወደ ሜዳ ይገባሉ።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
“ድጋሚ የመለያ ምት ዕድል ባገኝ ለመምታት ዝግጁ ነኝ”ጋብርኤል ማጋሌሽ
ቀይ ቀበሮዎቹ ቡሩንዲን 3ለ0 አሸነፈ
ወጣቶች ባላቸው እውቀት፣ እምቅ ችሎታና አቅም በተሰማሩበት ስራ መስክ ጠንክረው ከሰሩ ውጤታማ እንደሚሆኑ የዳውሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ገበየሁ ተናገሩ