የዴክላን ራይስ ትልቁ ውርርድ
እሁድ ዕለት አርሰናል እና ማንቸስተር ሲቲ ሲገናኙ፣ ጨዋታው ከሜዳ ላይ ፉክክር ባለፈ በርካታ መነጋገሪያ አጀንዳዎችን ተሸክሟል። ከሜዳ ውጭ ካሉ ጉዳዮች ባሻገር ግን፣ የጨዋታው ዋነኛ ትኩረት አንድ ተጫዋች ላይ ያርፋል ዴክላን ራይስ።
እ.ኤ.አ. በ2023 ራይስ ዌስትሃም ዩናይትድን ለመልቀቅ ሲወስን፣ በፊቱ ሁለት ትልልቅ ምርጫዎች ነበሩት በዋንጫዎች የደመቀው እና አስተማማኝ ስኬት የሚያስገኘው ማንቸስተር ሲቲ ወይስ ዳግም ወደ ክብር ለመመለስ በመገንባት ላይ የነበረው አርሰናል።
በወቅቱ ወደ ሰሜን ለንደኑ ክለብ ለማምራት መወሰኑ ትልቅ አደጋ ያለበት ውርርድ ተደርጎ ተወስዶ ነበር።
ከሦስት ዓመት ተኩል በኋላ ግን፣ ያ የራይስ ውሳኔ ትክክለኛነት በተግባር ተረጋግጧል።
ራይስ ወደ ኤምሬትስ ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ የቡድኑ ዋነኛ ሞተር እና መሪ በመሆን የመሀል ሜዳውን ሚዛን ቀይሮታል።
የእሱ መምጣት አርሰናልን ከተፎካካሪነት ወደ ጠንካራ የዋንጫ ባለቤትነት ተስፋ ከፍ ሲያደርገው፤ ለራሱም በዓለም እግር ኳስ ከሚገኙ ምርጥ አማካዮች ተርታ እንዲሰለፍ ትልቅ ዕድል ፈጥሮለታል።
የእሁዱ ፍልሚያ ሲጀመር ማንቸስተር ሲቲ ያመለጠውን ዕንቁ በተቃራኒ ማሊያ ሲመለከት፣ አርሰናል እና ዴክላን ራይስ ግን የዛሬ ሦስት ዓመት ተኩል የወሰዱት ድፍረት የተሞላበት ውሳኔ ያፈራውን ፍሬ ለዓለም ያሳያሉ።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ
የዴክላን ራይስ ትልቁ ውርርድ

More Stories
ከወራጅ ቀጣና ለመውጣት የሚደረግ ትንቅንቅ
ማንቸስተር ዩናይትድ የአምበሉን ብሩኖ ፈርናንዴዝ ውል በአንድ ዓመት አራዘመ
ቼልሲ አሌክስ ስኮትን ለማስፈረም ያለው ፍላጎት አሁንም ቀጥሏል