ማንቸስተር ዩናይትድ የአምበሉን ብሩኖ ፈርናንዴዝ ውል በአንድ ዓመት አራዘመ

ማንቸስተር ዩናይትድ የአምበሉን ብሩኖ ፈርናንዴዝ ውል በአንድ ዓመት አራዘመ

የእንግሊዙ ታላቅ ክለብ ማንቸስተር ዩናይትድ የቡድኑን ቁልፍ አማካይ እና አምበል ብሩኖ ፈርናንዴዝን በክለቡ የሚያቆየውን የአንድ ዓመት የውል ማራዘሚያ አንቀጽ ተግባራዊ ማድረጉ ተሰምቷል።

ዘ አትሌቲክ የክለቡን የውስጥ ምንጮች ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው፤ ፖርቹጋላዊው ኮከብ በነበረው ውል መሠረት የመጨረሻ ዓመት ላይ የነበረ ቢሆንም፣ ዩናይትድ ውሉን ለተጨማሪ 12 ወራት የማራዘም መብቱን ተጠቅሟል።

በዚህም መሠረት ብሩኖ ፈርናንዴዝ እስከ ሰኔ 2028 ድረስ በኦልድ ትራፎርድ የሚያቆየውን አዲስ ኮንትራት አግኝቷል።

በማንቸስተር ዩናይትድ የመሐል ሜዳ እንቅስቃሴ ውስጥ ወሳኝ ሚና ያለው ፈርናንዴዝ ውሉ መራዘሙ፣ ክለቡ ረጅም ጊዜያትን ታሳቢ ያደረገውን ዕቅድ ለማሳካት እና የቡድኑን መሪነት ለማስቀጠል ትልቅ እርምጃ መሆኑ ተገልጿል።

ዘጋቢ ፡ ሙሉቀን ባሳ