ቀይ ቀበሮዎቹ ቡሩንዲን 3ለ0 አሸነፈ

ቀይ ቀበሮዎቹ ቡሩንዲን 3ለ0 አሸነፈ



በሴካፋ ከ17 ዓመት በታች አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታውን ከቡሩንዲ ጋር ያከናወነው የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን 3ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።



በሩዋንዳ ኪጋሊ ፔሌ ስታዲየም ለኢትዮጵያ ታዳጊ ብሔራዊ ቡድን የድል ጎሎችን ዘሚካኤል ምንያህል፣አክረም አብዱሰላም እና አብዲሳ ጉተማ በመጀመሪያው አጋማሽ ከመረብ አሳርፈዋል።



በአሰልጣኝ ቤንጃሚን ዚመር የሚመሩት ቀይ ቀበሮዎቹ የምድብ ሁለተኛ የማጣሪያ ጨዋታቸውን የፊታችን ዕሮብ ከቀኑ 11 ሰዓት ላይ የሚያደርጉ ይሆናል።



ዘጋቢ፡ሙሉቀን ባሳ