የመስቀል በአል በጂንካ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ነው

የመስቀል በአል በጂንካ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ነው

በየዓመቱ መስከረም በመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ የሚከበረው የመስቀል በዓል በጂንካ ከተማ በተለያዩ መንፈሳዊ ትዕይንቶች እየተከበረ ይገኛል።

የግማደ መስቀሉ ሚስጢር የተገለጠበትን በዓል ለማክበርም የእምነቱ ተከታዮች መንፈሳዊ ሁነቱ በሚካሄድበት መስቀል አደባባይ ተገኝተዋል።

ከየአድባራቱ የተውጣጡ ካህናት፣ መዘምራንና የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች በዝማሬና በምስጋና ወደ ስፍራው ያቀኑ ሲሆን ዕለቱን የሚዘክሩ ስርአቶችንም እየከወኑ ይገኛል።

ዘጋቢ፡ ወንድሜነህ አድማሱ – ከጂንካ ጣቢያችን