ማንችስተር ዩናይትድ ሚካኤል ካርሪክን በሞሪሲዮ ፖቼቲኖ ለመተካት ከጫፍ መድረሱ ተገለፀ
ማንችስተር ዩናይትድ የወቅቱን ዋና አሰልጣኝ ሚካኤል ካርሪክን ከኃላፊነታቸው ለማሰናበት በሚያደርገው ዝግጅት፣ የአሜሪካ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ የሆኑትን ሞሪሲዮ ፖቼቲኖን በምትክነት ለማስፈረም ንግግር ማድረግ ጀምሯል።
ክለቡ በታሪኩ በ40 ዓመታት ውስጥ የከፋውን የውድድር ዘመን ጅምር በማስመዝገብ በወራጅ ቀጠናው ውስጥ የሚገኝ ሲሆን፤ የክለቡ የበላይ አካላት የአሰልጣኙን የወደፊት እጣ ፈንታ ለመወሰን አስቸኳይ ስብሰባ ላይ ይገኛሉ።
ሚካኤል ካርሪክ ረቡዕ ጠዋትም በካሪንግተን የልምምድ ማዕከል የተገኙ ቢሆንም፤ ከጀርባ ከፖቼቲኖ ጋር የሚደረጉ ንግግሮች መደረጋቸው ታውቋል።
በሌላ በኩል የዩናይትድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኦማር ቤራዳ እና የእግር ኳስ ዳይሬክተሩ ጄሰን ዊልኮክስ ከክለቡ ባለአክሲዮን ሰር ጂም ራትክሊፍ ጋር ለመገናኘት ወደ ሞናኮ አቅንተዋል።
ውይይቱ በመጀመሪያ የታቀደው የውድድር ዘመኑን ጅምር ለመገምገም የነበረ ቢሆንም፣ የካርሪክ ስንብት አሁን ላይ የስብሰባው ዋነኛ አጀንዳ ሆኗል።
ቤራዳ እና ዊልኮክስ የውሳኔ ሃሳባቸውን የእግር ኳስ ውሳኔዎችን ሙሉ በሙሉ ለሚቆጣጠሩት ሰር ጂም ራትክሊፍ ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ስካይ ስፖርትስ ባወጣው ዘገባ ማንችስተር ዩናይትድ አርጀንቲናዊውን አሰልጣኝ ሞሪሲዮ ፖቼቲኖን ከአሜሪካ ብሔራዊ ቡድን ጋር ከገባበት አዲስ ውል ለማላቀቅ 7 ሚሊየን ፓውንድ ገደማ የካሳ ክፍያ መክፈል ይጠበቅበታል።
ይህ የካሳ ክፍያ ለዩናይትድ አመራሮች መሰናክል እንደማይሆን ተገልጿል።
ፖቼቲኖ ዩናይትድን ለመረከብ ዝግጁ መሆናቸውን የገለፁ ቢሆንም፤ እስከ አሁን ባለው መረጃ መሠረት በመጪው ቅዳሜ አሜሪካ ከሄይቲ ጋር በምታደርገው ጨዋታ ቡድናቸውን ይመራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በኦልድ ትራፎርድ የካርሪክ የስንብት ቀናት ሊጠናቀቁ የተቃረቡ በሚመስሉበት በዚህ ወቅት፣ በሞናኮው ስብሰባ የሚወሰነው ውሳኔ በሰዓታት ውስጥ ይፋ ይሆናል ተብሎ ይገመታል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ
ማንችስተር ዩናይትድ ሚካኤል ካርሪክን በሞሪሲዮ ፖቼቲኖ ለመተካት ከጫፍ መድረሱ ተገለፀ

More Stories
ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ያደነቋቸው ማውሪሲዮ ፖቼቲኖ ወደ ዩናይትድ ሊመጡ?
የማንችስተር ዩናይትድ ባለቤቶች ክለቡን ለመሸጥ መወሰናቸው ተገለጸ
51 ቀይ ካርዶች የተመዘዙበት ጨዋታ