የመስቀል ደመራ በዓል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዲላ ከተማ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች እየተከበረ ነው‎

‎የመስቀል ደመራ በዓል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዲላ ከተማ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች እየተከበረ ነው
‎
‎በኢትዮጵያ በየዓመቱ በድምቀት ከሚከበሩ ሀይማኖታዊ በዓላት አንዱ የሆነው የደመራ በዓል በዲላ ሁለገብ ስታዲየም በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።
‎
‎ሥነ ሥርዓቱን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የጌዴኦ፣ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶሱ አባል ብፁዕ አቡነ ገሪማ በጸሎት አስጀምረዋል።
‎
‎በዓሉ የሀገረ ስብከት የመምሪያ አስተዳዳሪዎች፣ የአድባራት አስተዳዳሪዎች፣ የደብሩ ካህናት እና ዲያቆናት፣ የሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራንና የሃይማኖቱ ተከታዮች በተገኙበት በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።
‎
‎ዘጋቢ: እንግዳየሁ ቆሳ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን