በወላይታ ዞን ካዎ ኮይሻ ወረዳ በጤና ተቋም ለወላድ እናቶች እየተሰጠ ያለው አገልግሎት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱን ተጠቃሚ እናቶች ተናገሩ
የእናቶችና የሕፃናት ጤና አገልግሎትን ይበልጥ ለማሻሻል በትኩረት እየተሰራ መሆኑን በወላይታ ዞን ካዎ ኮይሻ ወረዳ ጤና ጣቢያ ገልዷል፡፡
ካነጋገርቸው እናቶች መካካል ወ/ሮ የምስራች አሸሎ ከላሾ 01 ቀበሌ ለ4ኛ ጊዜ ለወሊድ ክትትል መምጣታቸውን በመጠቆም ከባለሙያዎች በኩል በየጊዜዉ ግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት በሰፊው እየተሰጠ መቆየቱን በመግለጽ ይህ ክትትል ለእናትና ለልጁ ጤንነት ጥቅሙ የጎላ መሆኑን ገልጸዋል።
ሌላኛው ወ/ሮ ማርታ ኢልካ ላሾ ቄራ ቀበሌ ነዋሪ፤ ከወሊድ በፊት የክትትልና ድጋፍ አገልግሎት ማግኘታቸውን ገልፀው በተቋሙ በተደረገው ክትትል ሶስት ዙር በቂ እንክብካቤ በማግኘት በሠለጠነ ባለሙያ ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን ተናግረዋል።
አክለውም ከወሊድ ጋር ተያይዞ የሚሰጡ የእናቶችና የህፃናት ህክምና አገልግሎት በቀጣይም በተሟላ እና በትኩረት መሰራት እንዳለበት ተገልጋዮች ጠይቀዋል፡፡
እናቶች ደህንነታቸው የተጠበቀ የእርግዝና ጊዜ እና ወሊድ እንዲኖራቸው ከቅድመ-ወሊድ እስከ ድህረ-ወሊድ ባላው ሂደት ውሰጥ ሙያዊ ሀላፊነት በመወጣት በቂ ክትትልና እንክብካቤ እንደሚያደርጉ የገለጹት ደግሞ በጤና ጣቢያው አዋላጅ ባለሙያ ሲሰተር እድልነሸ እዮብ ናቸው።
በጤና ጣቢያው የእናቶችና ህፃናት ክፍል አስተባባሪ ፈቃዱ አየለ እንደሚሉት፤ በተቋሙ ደረጃ በ2019 ዓ.ም ከ3 ሺህ በላይ ለሚሆኑት እናቶች አገልግሎት ተሰጥቷቸዋል።
የላሾ ጤና ጣቢያ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አቤነይዘር ሴታ በበኩላቸው፤ ከዚህ በፊት በርካታ እናቶች እቤት በመውለድ ለሞትና ከወሊድ ጋር ተያይዞ በሚመጡ ችግሮች የሚጋለጡ መሆናቸውን አስረድተዋል።
አክለውም መንግስት በአሁኑ ወቀት የእናቶችንና ህፃናት ጤናማ ህይወት ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥርት ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት የተጠናከረ ድጋፍና ክትትል እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።
የወረዳው ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ቀልቱ በበኩላቸው፤ በየጤና ተቋማቱ የወሊድ ክትትልና ድጋፍ ሥራ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት በቅንጅታዊ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።
በወረዳ ደረጃ ሁለት ጤና ጣቢያ መኖሩን ጠቆሙት ኃላፊው ወሊድ እናቶች ከስምንት ወር ጀምሮ ማቆያን ጨምሮ ተዘጋጅቶላቸው ክትትልና ድጋፍ ሥራ እንደሚደረግም አመላክተዋል።
ዘጋቢ፡ ያሲን ጨተላ – ከዋካ ጣቢያችን

More Stories
ሊቨርፑል ወደ አሸናፊነት ሲመለስ ቼልሲ ሽንፈት አስተናገደ
የትምህርት ስርዓቱን የሚጎዱ የመልካም አስተዳደር ችግሮች በመስበር ትውልድን የመቅረፅ ስራ በአግባቡ መፈፀም ይገባል – የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ገዛኸኝ ጋሞ
በእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ 5 ጨዋታዎች ዛሬ ይካሄዳሉ