የዲላ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት 4ኛ ዙር 17ኛ አስቸኳይ ጉባኤ እያካሄደ ይገኛል‎

‎የዲላ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት 4ኛ ዙር 17ኛ አስቸኳይ ጉባኤ እያካሄደ ይገኛል
‎
‎ጉባኤው በዲላ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የከርሰ ምድር ውሃ ጉድጓድ ቁፋሮና አጠቃቀም ፈቃድ አሰጣጥና አፈጻጸም መመሪያ ላይ እንዲሁም በዲላ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ኮርፖሬሽን ቢዝነስ ኢንተርፕራይዝ ለማቋቋም በወጣ ደንብ ላይ እየመከረ ነው።
‎
‎በመጨረሻም የከተማ አስተዳደሩ የሥራ አስፈጻሚ አካላት ሹመት ቀርቦ ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
‎
‎ምክር ቤቱ እያካሄደ በሚገኘው ጉባኤ የምክር ቤቱ ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፈትለወርቅ በቀለ፣ የምክር ቤቱ አባላት፣ የዲላ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ መስፍን ደምሴ(ዶ/ር)፣ የኃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።
‎
‎ዘጋቢ: እንግዳየሁ ቆሳ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን