የመስቀል በዓልን ስናከብር የተቸገሩትን በመርዳትና ለሀገር ሰላም ዘብ በመቆም ሊሆን ይገባል – መጋቤ ሰናያት ያዕቆብ ደስታ
የመስቀል በዓልን ስናከብር የተቸገሩትን በመርዳትና ለአገር ሰላም ዘብ በመቆም ሊሆን እንደሚገባ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የጋሞና አካባቢው ሀገረ ስብከት ጸሐፊ መጋቤ ሰናያት ያዕቆብ ደስታ አሳሰቡ።
የመስቀል በዓል የሚከበርበትን ሃይማኖታዊና ታሪካዊ አመጣጥ ያብራሩት መጋቤ ሰናያት ያዕቆብ በወቅቱ አይሁድ በምቀኝነት የክርስቶስን መስቀል በቆሻሻ ስር ቀብረውት እንደነበር ገልጸዋል።
መስቀል የሰላም፣ የዕርቅና የመዳን ምልክት መሆኑን ያመለከቱት ጸሐፊው፤ ህዝበ ክርስቲያኑም ሆነ ሙሉው ማህበረሰብ ለሀገር ሰላም ዘብ ሊቆም እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል።
መጋቤ ሰናያት ያዕቆብ አክለውም በዓሉን ስናከብር በዙሪያችን ያሉ የተቸገሩ ወገኖችን በመደገፍና በመርዳት ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል።
በመጨረሻም መጋቤ ሰናያት ያዕቆብ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በዓሉ የሰላም፣ የፍቅርና የመተሳሰብ እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
ዘጋቢ: አዕላፍ አዳሙ – ከአርባ ምንጭ ጣቢያችን

More Stories
የመስቀል እና የደመራ በዓልን ስናከብር ኢየሱስ ክርስቶሰ በመስቀል ላይ የከፈለውን የደም ዋጋ በማሰብ ሊሆን ይገባል ሲሉ የወላይታ ዞን የኃይማኖት አባቶች አሳሰቡ
በበዓል ምክንያት በምርቶች ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ አቅማቸውን እየፈተነ በመሆኑ የሚመለከተው አካል ገበያውን እንዲያረጋጋ ያነጋገርናቸው የአርባምንጭ ከተማ ነዋሪዎች ጠየቁ
በዓሉ የክርስቶስ መስቀል የተገኘበትን አብነት በማድረግ በክርስቲያኖች ዘንድ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው መንፈሳዊ በዓል ነው – በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሀዲያና ስልጤ ሀገረ ስብከት ዋና ስራ አስኪያጅ