በዓሉ የክርስቶስ መስቀል የተገኘበትን አብነት በማድረግ በክርስቲያኖች ዘንድ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው መንፈሳዊ በዓል ነው – በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሀዲያና ስልጤ ሀገረ ስብከት ዋና ስራ አስኪያጅ
የመስቀል በዓል በአይሁድ ተቀብሮ የነበረ የክርስቶስ መስቀል የተገኘበትን አብነት በማድረግ በክርስቲያኖች ዘንድ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው መንፈሳዊ በዓል ነው ሲሉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሀዲያና ስልጤ ሀገረ ስብከት ዋና ስራ አስኪያጅ መልአከ ሕይወት ቀሲስ ንጉሴ ገለጹ።
በዓሉ ሲከበር የተቸገሩ ወገኖችን በመደገፍ በአብሮነት ሊሆን እንደሚገባ በመጠቆም በዓሉ የሠላምና የፍቅር እንዲሆን የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላልፈዋል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሀዲያና ስልጤ ሀገረ ስብከት ዋና ስራ አስኪያጅ መልዓከ ሕይወት ቀሲስ ንጉሴ ባወቀ እንደገለፁት፤ የመስቀል በዓል ክርስቶስ ተሰቅሎበት የነበረው መስቀል በሽታን ከመፈወስ ጀምሮ የተለያዩ ተዓምራቶችን ሲፈጽም የተመለከቱ አይሁዶች በቅናት ከቀበሩበት መገኘቱን ምክንያት በማድረግ የሚከበር መሆኑን አመላክተዋል።
የቆስጠንጢኖስ እናት ንግስት እሌኒ ባደረባት የመስቀል ፍለጋ ቁጭት በአረጋዊው ኪራኮስ ምክረ ሀሳብ በደመራ ጭስ ተመርታ ከተቀበረ 300 ዓመታት በላይ ያስቆጠረን የክርስቶስ መስቀል ማግኘቷን አስታውሰው፤ ሕይወት በደመራው የችቦዎች ህብረት የፈጠረው እምርታ በዘር በሃይማኖት መከፋፈል ቀርቶ በክርስቲያኖች ሁለንተናዊ አንድነት ሊንፀባረቅ ይገባል ብለዋል።
በዓሉ ሲከበር የተቸገሩ ወገኖችን በመደገፍ በአብሮነት ሊሆን እንደሚገባ በመጠቆም በዓሉ የሠላምና የፍቅር እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።
ዘጋቢ፡ አማኑኤል አጤቦ – ከሆሳዕና ጣቢያችን

More Stories
የመስቀል እና የደመራ በዓልን ስናከብር ኢየሱስ ክርስቶሰ በመስቀል ላይ የከፈለውን የደም ዋጋ በማሰብ ሊሆን ይገባል ሲሉ የወላይታ ዞን የኃይማኖት አባቶች አሳሰቡ
የመስቀል በዓልን ስናከብር የተቸገሩትን በመርዳትና ለሀገር ሰላም ዘብ በመቆም ሊሆን ይገባል – መጋቤ ሰናያት ያዕቆብ ደስታ
በበዓል ምክንያት በምርቶች ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ አቅማቸውን እየፈተነ በመሆኑ የሚመለከተው አካል ገበያውን እንዲያረጋጋ ያነጋገርናቸው የአርባምንጭ ከተማ ነዋሪዎች ጠየቁ