በዓላትን አስታኮ ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ ነጋዴዎችን የመቆጣጠር ስራ እየሰራ መሆኑን የሀድያ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ አስታወቀ
የሀዲያ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ተከተል ዶባሞ በዓሉን አስታኮ ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ ነጋዴዎችን በዞኑ በሁሉም መዋቅሮች የቁጥጥር እና ክትትል ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የመስቀል በዓልን ምክንያት በማድረግ ከወትሮ በተለየ መልኩ ሻጭና ሸማች የሚገናኙበት ወቅት መሆኑን የተናገሩት ኃላፊው ከሰንጋ ጀምሮ የእህልና ለበዓል ፍጆታ የሚያስፈልጉ ምርቶች በብዛት ካለበት በማስመጣት በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲቀርቡ መደረጉንም ገልጸዋል።
በዞኑ የተቋቋሙ የሰንበት ገበያዎችም ሸማችና ነጋዴን በቀጥታ እያገናኙ ዋጋን የማረጋጋት ስራ እየሰሩ ስለመሆኑም ተናግረዋል።
አንዳንድ ነጋዴዎች በበዓላት ወቅት ባዕድ ነገሮችን ቀላቅለዉ ሊሸጡ ስለሚችሉ ሸማቾች ለበዓል የሚያስፈልጉ ምርቶችን ሲገዙ በጥንቃቄ መሆን እንዳለበትም አቶ ተከተል አሳስበዋል።
በወፍጮ ቤቶች፣ በባልትና ውጤቶች መሸጫ፣ በእህል መጋዘኖችና በሱቆች ላይ ህገ-ወጥ ተግባራት እንዳይከናወን የክትትል ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነም ኃላፊው ገልጻዋል፡፡
ለመስቀል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉት አቶ ተከተል በዓሉ የአብሮነት፣ የፍቅር፣ የመተሳሰብ፣ የመረዳዳትና እና የብልጽግና እንዲሆን ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡
ዘጋቢ፡ ተሻለ ከበደ – ከሆሳዕና ጣቢያችን

More Stories
የመስቀል እና የደመራ በዓልን ስናከብር ኢየሱስ ክርስቶሰ በመስቀል ላይ የከፈለውን የደም ዋጋ በማሰብ ሊሆን ይገባል ሲሉ የወላይታ ዞን የኃይማኖት አባቶች አሳሰቡ
የመስቀል በዓልን ስናከብር የተቸገሩትን በመርዳትና ለሀገር ሰላም ዘብ በመቆም ሊሆን ይገባል – መጋቤ ሰናያት ያዕቆብ ደስታ
በበዓል ምክንያት በምርቶች ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ አቅማቸውን እየፈተነ በመሆኑ የሚመለከተው አካል ገበያውን እንዲያረጋጋ ያነጋገርናቸው የአርባምንጭ ከተማ ነዋሪዎች ጠየቁ