በኮሬ ዞን የአደጋ ስጋት መከላከልና በምግብ ራስን የመቻል ተግባር ዙሪያ የውይይት መድረክ ተካሄደ
የአደጋ ስጋት ለመከላከልና ለሰብዓዊ ድጋፍ በደህና ጊዜ ሀብት መሰብሰብ ለክፉ ቀን ዋስትና ነው ተብሏል፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአደጋ ስጋትና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ወገኔ ብዙነህ፤ ከተረጂነት ተላቆ በምግብ እራስን ለመቻልና የአደጋ ስጋትን ለመከላከል ተረጂዎችን በየዘርፉ መለየትና ለአደጋ ስጋት የማይበገር ክልል ለመፍጠር በትኩረት መሥራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡
በክልሉ የከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አፈወርቅ ለማ በበኩላቸው፤ ከውጭ የሚጠበቅ እርዳታ እንደሌለ በመግለጽ ራስን በራስ ለመቻል የሰብዓዊ ድጋፍ ተግባር ለመጠባበቂያና ለዕለት ደራሽ በዘላቂነት ማከናወን እንደሚገባ አስረድተዋል።
የኮሬ ዞን አደጋ ስጋት ሥራ አመራር እና ምግብ ዋስትና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ከፍያለው አዱላ፤ በዞኑ ከቤት ንብረታቸው እና በከፊል ከእርሻቸው የተፈናቀሉ ሰብዓዊ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው 12 ሺህ 182 የህብረተሰብ ክፍሎች መለየቱን ተናግረዋል።
ሰብዓዊ ድጋፉም በአይነትና በካሽ የሚሰበሰብ ሲሆን 19 ሺህ 300 ኩንታል ለመሰብሰብ ታቅዶ እስካሁን ወደ 283 ኩንታል የሚጠጋ እህል መሰብሰቡን የተናገሩት አቶ ከፍያለው፤ በካሽ 40 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 3 ሚሊየን 342 ሺህ ብር መሰብሰቡን ገልፀዋል፡፡
ለመጠባበቂያ ፈንድ ድጋፍ አሰባሰብ በወጣው ደንብ ቁጥር 112/2018 መሠረት ከሁለም ማህበራዊ መሠረቶች፣ ከቋሚ ንብረት ሽያጭና፣ ከሀይማኖት ተቋማት፣ ከባለበጀት መሥሪያ ቤቶች፣ ከመንግሥት ተሿሚዎችና ሠራተኞች፣ ከልማት ድርጅቶች፣ ከንግዱ ማህረሰብ፣ ከሲቪክ ማህበራትና አርሶናአርብቶ አደሮች በተለያየ ደረጃ ለመሰብሰብ ታቅዶ እየተሠራ ነው ብለዋል።
ከድጋፍ እርሻ አኳያ በዞን ደረጃ 241 ሄክታር የታረሰ ሲሆን ከ93 ሄክታር በላይ ታርሶ 9 ነጥብ 3 ሄክታር በዘር የተሸፈነ ቢሆንም የዝናብ እጥረት ስጋት መኖሩን አቶ ከፍያለው ገልጸዋል።
በአጠቃላይ ለመጠባበቂያና ዕለት ደራሽ የሀብት አሰባሰብ ተግባር ያለበት ደረጃና ለሰብዓዊ ድጋፍ ምርት የታረሱ የእርሻ ማሳ ጉብኝት ተደርጓል።
ዘጋቢ፡ ምርጫ መላኩ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን

More Stories
የመስቀል በዓልን ስናከብር የተቸገሩትን በመርዳትና ለሀገር ሰላም ዘብ በመቆም ሊሆን ይገባል – መጋቤ ሰናያት ያዕቆብ ደስታ
በበዓል ምክንያት በምርቶች ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ አቅማቸውን እየፈተነ በመሆኑ የሚመለከተው አካል ገበያውን እንዲያረጋጋ ያነጋገርናቸው የአርባምንጭ ከተማ ነዋሪዎች ጠየቁ
በዓሉ የክርስቶስ መስቀል የተገኘበትን አብነት በማድረግ በክርስቲያኖች ዘንድ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው መንፈሳዊ በዓል ነው – በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሀዲያና ስልጤ ሀገረ ስብከት ዋና ስራ አስኪያጅ