በየጊዜው የሚደረጉ የስራ ግምገማዎችና ምዘና ስራዎች ተቋሙ ተልዕኮውን በአግባቡ እንዲወጣ አስተዋጽኦ ማበርከቱ ተገለፀ
በደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የሚዛን ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አመራርና ስራተኞች መካከል ሲደረግ የነበረው ተቋማዊ የግምገማ መድረክ ተጠናቋል፡፡
በመድረኩ ማጠቃለያ የቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ትዕዛዙ ኬንጫ፤ ለአራት ቀናት በተቋሙ ሲደረግ የነበረው አጠቃላይ ተቋማዊ የስራ ግምገማ መድረክ በስኬት መጠናቀቁን አንስተዋል።
የ2018 በጀት አመት ስራዎችን አፈፃፀም መነሻ በማድረግ የተቋሙ አመራርና አጠቃላይ ሰራተኞች ድርሻ ምን ይመስል እንደነበር ለማሳየት የግምገማ መድረኩ መዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡
በግምገማው አጠቃላይ ሰራተኞች እርስ በእርሳቸው ያሉባቸውን የመፈፀም ክፈተቶች መለየት ያስቻለ ውጤታማ መድረክ እንደነበር አንስተው፤ በተቋማት ውስጥ በየጊዜው የሚደረጉ የስራ ግምገማዎች ተቋሙ ተልዕኮውን አበግባቡ እንዲወጣ አስተዋጽኦ እንዳለው አቶ ትዕዛዙ ጠቁመዋል፡፡
በቀጣይ የተቋሙ ሰራተኞች የነበሩባቸውን ጉድለቶች በማረም በተያዘው በጀት አመት ውጤታማ ስራዎችን ለመፈፀም መነሳሳት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
በተቋሙ ባለፉት አመታት ከይዘት እና አቀራረብ ጋር የሚያያዙ ችግሮች ስለመኖራቸው በግምገማው መነሳቱን የተናገሩት ስራ አሰኪያጁ፤ እያንዳንዱ ሰራተኛ በቀጣይ በጀት አመት ሰራውን በአግባቡ መወጣት እንዳለበት ገልፀዋል።
የተቋሙ ምክትል ስራ አስኪያጅ እና የይዘት ዘርፍ ኃላፊ አቶ መኮንን ኢያርዝ በበኩላቸው፤ እንደተቋም የተደረገው የግምገማ መድረክ ወቅታዊ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የተቋሙ ሰራተኞች የአፈፃፀም ብቃትና ደረጃ ለማሳደግ የሚያግዝ መሆኑን ተናግረዋል።
የሚዲያ ተቋሙ በበጀት አመቱ ውጤታማ ስራዎች ማከናወን እንዲችል ሁሉም ጋዜጠኛ ተቀናጅቶና ተቀራርቦ በአንድነት መስራት እንደሚጠበቅባቸው ገልጸዋል።
አሁን ላይ ተቋሙ ለህብረተሰቡ የመረጃ ምንጭ በመሆን በርካታ ስራዎችን እየሰራ ነው ያሉት አቶ መኮንን፤ ጣቢያው ከተለያዩ ተቋማት ጋር ተቀራርቦ በመስራት እና የውስጥ ገቢን ለማሳደግ ቅንጅታዊ አሰራር አጠናክሮ ማስቀጠል ያስፈልጋልም ብለዋል።
በግምገማ መድረኩ ላይ ከተሳተፉ ጋዜጠኞች መካከል ጋዜጠኛ ተረፈ ጎባብ፣ ጋዜጠኛ ዳክራሻ ሲር፣ ጋዜጠኛ ይሁኔ መለስ እና ጋዜጠኛ ሂሩት ያሲን በሰጡት አስተያየት፤ በተቋሙ የተደረገው የግምገማ መድረክ ጥሩ መገነባባት ያገኙበት እና ጉድለታቸውን ለመለየት አቅም እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል፡፡
በተቋሙ የተካሄደው ግምገማ ለቀጣይ ስራዎች በተነሳሽነት ለመፈፀም ጥሩ መነቃቃት እንደፈጠረባቸው ባለሙያዎቹ ጠቁመዋል።
ዘጋቢ፡ ተመስገን ዳጉሳ – ከሚዛን ጣቢያችን

More Stories
ሰው ተኮር የበጎነት እሴቶች በሁሉም አካባቢዎች ተደራሽ እንዲሆኑ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ላይ ይገኛል – ዶ/ር መሀመድ ኑሪዬ
በዓልን ምክንያት በማድረግ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ እንዳይደረግ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
የጎፋና ኦይዳ ህዝቦች የባህል፣ የታሪክና የቋንቋ ሲምፖዚየም በሳውላ ከተማ እየተካሄደ ነው