የጎፋና ኦይዳ ህዝቦች የባህል፣ የታሪክና የቋንቋ ሲምፖዚየም በሳውላ ከተማ እየተካሄደ ነው

የጎፋና ኦይዳ ህዝቦች የባህል፣ የታሪክና የቋንቋ ሲምፖዚየም በሳውላ ከተማ እየተካሄደ ነው

የጎፋና ኦይዳ ህዝቦች የዘመን መለወጫ በዓል የሆነው “የጎፋ ጋዜ” እና “የኦይዳ ዮኦ” በዓል ምክንያት በማድረግ የባህል፣ የታሪክና ቋንቋ ስምፖዚየም በሳውላ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በሲምፖዚየሙ ላይ የበዓሉን አከባበር ለቀጣይ ትውልድ ለማስተላለፍ በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ጥናታዊ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግ ይጠበቃል።

“የጎፋ ጋዜ” እና “የኦይዳ ዮኦ” በዓል የሰላም የይቅርታ የፍቅርና የወንድማማችነት በዓል ነው።

በመድረኩ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የወላይታ ሶዶ ክላስተር አስተባባሪና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተፈሪ አባተን ጨምሮ ከፌደራል፣ ከክልል፣ ከዞኑ እና ከተለያዩ አካባቢዎች የተውጣጡ ከፍተኛ አመራሮች፣ ምሁራን፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ወጣቶችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ ነው።

ዘጋቢ፡ አይናለም ሰለሞን – ከሳውላ ጣቢያችን