ጥራት ያለው ቡና የአርሶ አደሮችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሚናው የጎላ መሆኑን በጌዴኦ ዞን የይርጋጨፌ ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት አስታወቀ
በ2019 ምርት ዘመን ጥራት ያለውን ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብና የአርሶ አደሮችን ተጠቃሚነት ለማሳደግ አቅዶ እንደሚሰራ የይርጋጨፌ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ድጋፌ ሙላቱ ገልጸዋል።
በምርት ዘመኑ ወረዳው ከ42 ቶን በላይ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ እቅድ ይዞ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝና ይህንን እቅድ ለማሳካት ከ40 በላይ የእሸት ቡና መፈልፈያ ኢንዱስትሪዎች ዝግጅታቸውን ጨርሰው ወደ ስራ መግባታቸውን ገልጸዋል።
የይርጋጨፌ ኦርጋኒክ ባለልዩ ጣዕም ቡና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተፈላጊ በመሆኑ አርሶ አደሮች በጥንቃቄ እንዲሰበስቡና ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
የሰብል ባለሙያዎች አቶ ሽፈራው ሮቤ እና መስፍን ገረመው ከአርሶ አደሮች ጎን ሆነው ትምህርት በመስጠት በምርት ዘመኑ ጥራት ያለውን ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ በሚደረገው ጥረት ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ አብራርተዋል።
አቶ አለመ ብረካ፣ ገረሙ ደያሶ እና ሌሎችም ሃሳባቸውን ከሰጡ አርሶ አደሮች መካከል ሲሆኑ ለ2019 ምርት ዘመን ከግብርና ባለሙያዎች በተቀበሉት ትምህርት የምርት ገቢ ከማሳደግ ጀምሮ ለኢንዱስትሪ የሚሆነውን ቡና መሰብሰብ መጀመራቸውን ገልጸዋል።
የቡና ምርት ጥራቱን በጠበቀ ሁኔታ እንዲቀርብና የአርሶ አደሩም ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ሁላችንም ኃላፊነት መወጣት አለብን ብለዋል።
ዘጋቢ፡ እስራኤል ታደሰ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
ጥራት ያለው ቡና የአርሶ አደሮችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሚናው የጎላ መሆኑን በጌዴኦ ዞን የይርጋጨፌ ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት አስታወቀ

More Stories
የጎፋና ኦይዳ ህዝቦች የባህል፣ የታሪክና የቋንቋ ሲምፖዚየም በሳውላ ከተማ እየተካሄደ ነው
የግብርና ቴክኖሎጂን በማስፋት አርሶ አደሩ ለገበያ የሚተርፍ ምርት እያመረተ መሆኑ ተገለጸ
መሳላ የሕዝቦችን ትስስር፣ አንድነትና መከባበርን የሚያጎለብት ታላቅ በዓል ነው – የተለያዩ ብሔር ብሔረሰብ ተወካዮች