የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) የ”ያሆዴ” በዓልን ስናከብር ስለ ሀገራችን ልማትና ስለ ህዝባችን አብሮነት የበለጠ የምንተጋበት ወቅት ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል
የ”ያሆዴ” በዓል በሆሳዕና ሀዲይ ነፈራ በልዩ ልዩ ሁነቶች እየተከበረ ነው።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር) በ”ያሆዴ” በዓል ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ”ያሆዴ” የክረምት ወቅት ጨለማ ሳይሆን ፈጣሪ ያስቀመጠው የጊዜ ቀመር እና የብሩህ ተስፋ መሸጋገሪያ ወቅት መሆኑን ገልጸዋል።
በዓሉን ስናከብር ከተለመደው ስብሰባና ድምቀት ባለፈ ለአብሮነት እና ለጋራ ምክክር ሊውል እንደሚገባ ያነሱት ዶ/ር እንዳሻው፤ የሀገራችንን ሰላም፣ የህዝባችንን አንድነት እና አብሮነት የበለጠ የምናጠናክርበት ወቅት ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል።
በዘንድሮው ዓመት በሀገራችንና በክልላችን የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን አጠናክሮ በመቀጠል ለህዝብ ተጠቃሚነት በቁርጠኝነት መትጋብ እንደሚገባም ርዕሰ መስተዳድሩ አመላክተዋል።
በመጨረሻም የዘንድሮው የ”ያሆዴ” በዓል የሰላም፣ የአብሮነት እና የፍቅር እንዲሆን የተመኙት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ ለበዓሉ በምረቃና በድምቀት መከበር በሙያቸው እና በዕውቀታቸው ድጋፍ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።
ዘጋቢ፡ ሄኖስ ካሳ – ከሆሳዕና ጣቢያችን

More Stories
መሳላ የሕዝቦችን ትስስር፣ አንድነትና መከባበርን የሚያጎለብት ታላቅ በዓል ነው – የተለያዩ ብሔር ብሔረሰብ ተወካዮች
የሀድያ ብሔር ዘመን መለወጫ “ያሆዴ” በዓል ከብሔሩ ዘመን መለወጫነት ባሻገር የሚያበረክተው ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ የጎላ ነው – የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማቴዎስ አኒዮ
የጠምባሮ ብሔረሰብ የባህል፣ የታሪክና ቀንቋ ሲምፖዚየም በሙድላ ከተማ እየተካሄደ ነው