የጠምባሮ ብሔረሰብ የባህል፣ የታሪክና ቀንቋ ሲምፖዚየም በሙድላ ከተማ እየተካሄደ ነው
የጠምባሮ ብሔር በራሱ የቀን መቁጠሪያ ቀመር አዲሱን አመት የሚቀበልበት የመሪሾ መሳላ በአል አብሮነትን፣ ምስጋናን፣ ደስታን፣ መተሳሰብን፣ ይቅርታንና ፍቅርን የሚያንፀባርቅ የብሔሩ ዋነኛ መገለጫ ነው።
በአሉ “ባህላችንን ከትውልድ ወደ ትውልድ አንድነታችንን ከዛሬ ወደ ነገ” በሚል መሪ ሀሳብ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተካሄደ ነው።
በአሉን አስመልክቶ በተዘጋጀው ሲምፖዚየም ላይ የብሔሩን ቋንቋ እና ባህል የሚመለከት ውይይት እየተደረገ ነው።
ሲምፖዚየሙ የብሔሩን ባህል፣ ታሪክ እና እሴቶች ጠንቅቆ የሚያውቅ ትውልድ ለመፍጠር ያለመ ነው።
በሲምፖዚየሙ ላይ የፌደራል፣ የክልል እና የልዩ ወረዳው የመንግስት ኃላፊዎች እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ዘጋቢ፡ ቴዎድሮስ ወርቅነህ

More Stories
መሳላ የሕዝቦችን ትስስር፣ አንድነትና መከባበርን የሚያጎለብት ታላቅ በዓል ነው – የተለያዩ ብሔር ብሔረሰብ ተወካዮች
የሀድያ ብሔር ዘመን መለወጫ “ያሆዴ” በዓል ከብሔሩ ዘመን መለወጫነት ባሻገር የሚያበረክተው ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ የጎላ ነው – የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማቴዎስ አኒዮ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) የ”ያሆዴ” በዓልን ስናከብር ስለ ሀገራችን ልማትና ስለ ህዝባችን አብሮነት የበለጠ የምንተጋበት ወቅት ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል