የሀዲያ ብሔር ዘመን መለወጫ “ያሆዴ” በዓል በሀዲይ ነፈራ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል

የሀዲያ ብሔር ዘመን መለወጫ “ያሆዴ” በዓል በሀዲይ ነፈራ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል

በበዓሉ መርሃ ግብር የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)፣ በብልጽግና ፓርቲ የክልሉ ብልጽግና ፖርቲ ቅርንጫፍ ጸህፈት ቤት ኃላፊ ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር)፣ የሀድያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማቴዎስ አኒዮ፣ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የባህል ሽማግሌዎች፣ ከሀገሪቱ ከተለያዩ አካባቢዎች የተጋበዙ እንግዶች፣ የብሔሩ ተወላጆችና ሌሎችም ታዳሚዎች እየታደሙ ይገኛል።

በዓሉ በተለያዩ ባህላዊ ክዋኔዎች ታጅቦ በሀዲይ ነፈራ በታላቅ ድምቀት እየተከበረ ነው፡፡

ዘጋቢ፡ ኤርጡሜ ዳንኤል – ከሆሳዕና ጣቢያችን