የከምባታ ብሄር ዘመን መለወጫ ‘መሳላ’ በዓል በዱራሜ ሁለገብ ስታዲየም በድምቀት እየተከበረ ነው
ሀዋሳ፡ መስከረም 12/2019 ዓ.ም (ደሬቴድ) የከምባታ ብሄር ዘመን መለወጫ ‘መሳላ’ በዓል “መሳላ ለጋራ እድገታችን” በሚል መሪ ቃል በዱራሜ ሁለገብ ስታዲየም በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።
በበዓሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ፋጤ ስርሞሎን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የዞኑ አስተዳዳሪ፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንዲሁም የዱራሜ ከተማ ነዋሪዎችና ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ የብሄሩ ተወላጆች ታድመዋል፡፡
ዘጋቢ፡ ሀብትነህ ሰንበቶ

More Stories
መሳላ የሕዝቦችን ትስስር፣ አንድነትና መከባበርን የሚያጎለብት ታላቅ በዓል ነው – የተለያዩ ብሔር ብሔረሰብ ተወካዮች
የሀድያ ብሔር ዘመን መለወጫ “ያሆዴ” በዓል ከብሔሩ ዘመን መለወጫነት ባሻገር የሚያበረክተው ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ የጎላ ነው – የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማቴዎስ አኒዮ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) የ”ያሆዴ” በዓልን ስናከብር ስለ ሀገራችን ልማትና ስለ ህዝባችን አብሮነት የበለጠ የምንተጋበት ወቅት ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል