“አተካን ሂሞ” (የአተካና ምሽት) በተለያዩ ባህላዊ ስነ ስርአቶች በሆሳዕና ከተማ በሀዲይ ነፈራ በድምቀት ተከብሯል
በሀዲያ ብሔር ባህል መሠረት ከእርድ ቀን አስቀድሞ የሚከበረው አተካን ሂሞ ወይም “የአተካና ምሽት” በመባል የሚታወቀው የአተካና እራት የመብላት ሥነ-ሥርዓት በሆሳዕና ከተማ በሀዲይ ነፈራ ተካሂዷል።
አተካና የሀዲያ ብሔር ዘመን መገለጫ ከሆኑ ባህላዊ ምግቦች መካከል አንዱ ሲሆን፣ በያሆዴ በዓል ከሚዘጋጁ ባህላዊ የምግብ ዓይነቶች ውስጥ በዋናነት የሚጠቀስ ነው።
ምግቡ በብሔረሰቡ ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው በመሆኑ ከአሠራሩ ጀምሮ እስከሚቀርብበት ዕቃ ድረስ የራሱ የሆነ ሥርዓት አለው።
“ያሆዴ” የተጣላ የሚታረቅበት፣ የፍቅር፣ የመተሳሰብ እና የአብሮነት በዓል መሆኑንም በስነስርዓቱ ላይ የታደሙ እድምተኞች ገልጸዋል።
ዘጋቢ: በየነ ሰላሙ – ከሆሳዕና ጣቢያችን

More Stories
መሳላ የሕዝቦችን ትስስር፣ አንድነትና መከባበርን የሚያጎለብት ታላቅ በዓል ነው – የተለያዩ ብሔር ብሔረሰብ ተወካዮች
የሀድያ ብሔር ዘመን መለወጫ “ያሆዴ” በዓል ከብሔሩ ዘመን መለወጫነት ባሻገር የሚያበረክተው ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ የጎላ ነው – የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማቴዎስ አኒዮ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) የ”ያሆዴ” በዓልን ስናከብር ስለ ሀገራችን ልማትና ስለ ህዝባችን አብሮነት የበለጠ የምንተጋበት ወቅት ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል