ክርስቲያኖ ሮናልዶ እና ጆርጂና ሮድሪጌዝ የጋብቻ ስነ ስርዓታቸውን ፈፀሙ
ፖርቹጋላዊው ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ የረጅም ጊዜ ፍቅረኛው ከሆነችው ጆርጂና ሮድሪጌዝ ጋር በትውልድ ሀገሩ ፖርቱጋል ህጋዊ የጋብቻ ስነ-ስርዓታቸውን ፈፅመዋል።
ከዋና ከተማዋ ሊዝበን በስተምዕራብ 20 ማይልስ ያህል ርቃ በሚትገኘው ካስካይስ በተባለችው የባህር ዳርቻ ከተማ በተካሄደው በዚህ የሰርግ ስነ-ስርዓት ላይ አምስቱ ልጆቻቸው እና የቅርብ ቤተሰቦቻቸው ተገኝተዋል።
ጥንዶቹ የጋብቻ ቀለበታቸውን የሚያሳይ ምስል በኢንስታግራም ገጻቸው ላይ በማጋራት ደስታቸውን ለደጋፊዎቻቸው አብስረዋል።
እ.ኤ.አ በ2016 በማድሪድ ከተማ ከተዋወቁ በኋላ ላለፉት አስር ዓመታት አብረው የዘለቁት ሮናልዶ እና ጆርጂና፣ ጋብቻቸውን የፈጸሙት የሮናልዶ ክለብ አል ናስር አዲሱን የ2026-27 የሳዑዲ ፕሮ ሊግ የውድድር ዘመን ከመጀመሩ ከአራት ቀናት በፊት ነው።
በእግር ኳስ ተጫዋችነቶ ዘመኑ ለስፖርቲንግ ሊዝበን፣ ማንችስተር ዩናይትድ፣ ሪያል ማድሪድ፣ ጁቬንቱስ፣ አል ናስር እና ለፖርቱጋል ብሔራዊ ቡድን በመጫወት በርካታ ክብረወሰኖችን ያስመዘገበው ሮናልዶ፣ እስካሁን ወደ 1,000 የሚጠጉ ግቦችን አስቆጥሯል።
በቅርቡ በስድስተኛው የዓለም ዋንጫ ላይ በመሳተፍ ከሊዮኔል ሜሲ ጋር የነበረውን የበርካታ የዓለም ዋንጫዎች ተሳትፎ ክብረወሰን የተጋራው ሮናልዶ፣ ያደረገው ጨዋታ የመጨረሻው የዓለም ዋንጫው መሆኑን አረጋግጧል።
ሆኖም ከፖርቱጋል ብሔራዊ ቡድን ሙሉ በሙሉ ስለመገለሉ እስካሁን የሰጠው ውሳኔ የለም።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
ሶማሊያዊው ዳኛ ኦማር አርታን የዩኤፋ ሱፐር ካፕን በዋና ዳኝነት በመምራት የመጀመሪያው አፍሪካዊ ሊሆኑ ነው
አርሰናል ብሩኖ ጊማራኤሽን በይፋ አስፈረመ
ሪያል ማድሪድ ያን ዲዮማንዴን በታሪካዊ የዝውውር ክፍያ አስፈረመ