የሊቢዶ ማረቆ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ ‘ፊተቴ’ በዓል በቆሼ ከተማ በታላቅ ድምቀት እየተከበረ ይገኛል
የሊቢዶ ማረቆ ብሔረሰብ ባህላዊ እሴት የሆነው ‘ፊተቴ’ ዕርቀ ሰላም የሚወርድበት፣ የተበደሉ የሚካሱበትና ጎዶሎው ሞልቶ በሙሉነት ወደ አዲሱ ዓመት የሚሸጋገሩበት፣ የሰላም፣ የፍቅር፣ የአብሮነት፣ የሕዝቦች አንድነትና የታላቅነት መገለጫ በዓል እንደሆነ ተመላክቷል።
የሀፋ ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች ምርቃት እንዲሁም የብሔረሰቡ ባህላዊ ክዋኔዎች የበአሉ ታላቅ ድምቀት ነበሩ።
በበአሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ አመራሮች፣ የማረቆ ልዩ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ጀማል አማሮን ጨምሮ ሌሎች በየደረጃው የሚገኙ ኃላፊዎች፣ በክልሉ ውስጥ የሚገኙ የሁሉም ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ተወካዮች እንዲሁም የማረቆ ብሔረሰብ ተወላጆች በበአሉ ታድመዋል።
ዘጋቢ፡ ሀብታሙ እንግዳው

More Stories
ፈጣን፣ ወቅታዊና ተአማኒ መረጃዎችን ለሕብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ እየሠራ መሆኑን በደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የሳውላ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ገለጸ
በ248 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነቡ 3 የሕክምና አገልግሎት ማዕከላት በአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ተመረቁ
የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄ በጥራትና በፍጥነት መመለስ ለነገ የማይባል ከአመራሩ የሚጠበቅ ስራ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ፍቅሬ አማን ገለፁ