አርሰናል ብሩኖ ጊማራኤሽን በይፋ አስፈረመ
የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል አማካዩን ብሩኖ ጊማራኤሽን ከኒውካስል ዩናይትድ በ75 ሚሊዮን ፓውንድ የዝውውር ዋጋ ማስፈረሙን በይፋ አረጋግጧል።
ዕድሜው 28 ዓመት የሆነው የብራዚል ብሔራዊ ቡድን አማካይ፣ በኤምሬትስ ለተጨማሪ አንድ ዓመት የማራዘም አማራጭ ያለው የ4 ዓመት ኮንትራት ፈርሟል።
ወደ መድፈኞቹ መቀላቀሉን ተከትሎ አስተያየቱን የሰጠው ጊማራኤሽ “ከአንድሪያ ቤርታ እና ከሚኬል አርቴታ ጋር ከተነጋገርኩበት ጊዜ አንስቶ በጣም ተደስቼ ነበር። በሕይወቴ አዲስ ፈተና እንደሚያስፈልገኝ ውስጤ ይነግረኝ ነበር፤ የአርሰናል ተጫዋች መሆን ደግሞ ለሕይወቴ አሪፍ አዲስ ፈተና ነው ብዬ አስባለሁ” ሲል ተናግሯል።
ተጫዋቹ አክሎም “አርሰናልን በመቀላቀሌ እጅግ ተደስቻለሁ። ምርጥ ብቃቴን ለመስጠት ቃል እገባለሁ፣ አብረን ብዙ ጥሩ ትዝታዎችን እንደምንፈጥር ተስፋ አደርጋለሁ” ብሏል።
የአርሰናል የስፖርቲንግ ዳይሬክተር አንድሪያ ቤርታ በበኩላቸው “ብሩኖ ጊማራኤሽን ወደ ክለባችን በማስፈረማችን እጅግ ደስ ብሎናል። ብሩኖ ድንቅ የአእምሮ ጥንካሬ እና ከፍተኛ ብቃት ያለው ተጫዋች ሲሆን ለቡድናችን ጠንካራ መሪነትን ይዞ ይመጣል” ብለዋል።
ይህ ከፍተኛ የገንዘብ ወጪ የተደረገበት ዝውውር አርሰናል በመጪው የውድድር ዘመን የተሻለ ውጤት ለማስመዝግብና ለዋንጫ ያለውን ትልቅ አላማ እና ዝግጅት የሚያሳይ እንደሆነ ተገልጿል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
ሪያል ማድሪድ ያን ዲዮማንዴን በታሪካዊ የዝውውር ክፍያ አስፈረመ
ብሩኖ ጊማሬስ የሕክምና ምርመራውን በስኬት አጠናቀቀ
9 ክለቦች በአዲስ አሰልጣኞች ፍልሚያቸውን የሚጀምሩበት የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ