ኢትዮጵያ እየመከረች ነው!
የሐምሌ 14 ቀን 2018 ዓ.ም የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ዐበይት መረጃዎች
በትናንትናው ዕለት በቡድን ተከፋፍለው መመካከር የጀመሩት ተመካካሪዎች ዛሬም በየቡድናቸው በመሆን መመካከር ቀጥለዋል፡፡
50 ተመካካሪዎችን በመያዝ በ80 ቡድን ተከፋፍለው መመካከር የጀመሩት ንዑሳን ቡድኖች በተሟላ ሁኔታ ከትላንት ከሰዓት ጀምሮ በየንዑስ ቡድናቸው አስር አስር በመሆን ምክክር በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ ይህ ሂደት እስከ ነገ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
በዚህ ሂደት ተመካካሪዎች በሚመካከሩባቸው የአጀንዳ ሃሳቦች ላይ በርካታ ሃሳቦችን እና ምልከታዎችን በማቅረብ ላይ ይገኛሉ፡፡
ሂደቱ ተመካካሪዎች ላለመግባባት መንስኤ የሆኑ እጅግ መሰረታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ያሉ አመለካከቶችን እና ምክንያቶችን ከስር መሰረቱ አንዳቸው ሌላቸውን እንዲረዱ መደላድል እንደሚፈጥር ይጠበቃል፡፡
ይህንን ሂደት ለማሳካት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከተለያዩ ተቋማት በሙያቸው፣ በትምህርት ዝግጅታቸው እና ለአጀንዳ ሃሳቦቹ ባላቸው ሙያዊ ቅርበት ብቁ ናቸው ብሎ ያመነባቸው 80 የሚጠጉ የባለሙያዎች ስብስብ (Panel of Experts) በማሰባሰብ በሀገራዊ ምክክር ጉባኤው ላይ እያሳተፈ ይገኛል፡፡
የባለሙያዎች ስብስብ በአጀንዳ ነጥቦች ላይ ለሚፈጠሩ ብዥታዎች ማብራሪያ በመስጠት ሂደቱን በመደገፍ ላይ ይገኛሉ፡፡
በሌላ በኩል በዚህ የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የተለያዩ የሀገር ውስጥ ተቋማት ሂደቱን ለመታዘብ ለኮሚሽኑ ጥያቄ ባቀረቡት መሰረት ከኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጥምረት፣ ከተለያዩ የሙያ ማህበራት፣ ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ እና ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የተውጣጡ ከ50 በላይ ገለልተኛ ታዛቢዎች የምክክር ሂደቱን እየታዘቡ ይገኛሉ፡፡
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን
ሐምሌ 14 ቀን 2018 ዓ.ም

More Stories
ምክር ቤቱ በህዝቡ ህይወት ላይ የሚታይ ለውጥ ለማምጣት እየሰራ እንደሚገኝ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ካሰች ኤሊያስ ገለጹ
የኩታ ገጠም የአስተራረስ ስርአትን በመጠቀም የግብርናውን ዘርፍ ማዘመንና ምርታማነትን ማሳደግ ወሳኝ መሆኑን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪና የግብርና ቢሮ ሀላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር ገለፁ
በኢትዮጵያ በሚቀጥሉት ዓመታት ለሚደረጉ የኢንዱስትሪ ሽግግሮች ግብርና መሠረት ነው ሲሉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የመንግስት ዋና ተጠሪና በብልጽግና ፓርቲ የክልሉ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ ተናገሩ