ምክር ቤቱ በህዝቡ ህይወት ላይ የሚታይ ለውጥ ለማምጣት እየሰራ እንደሚገኝ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ካሰች ኤሊያስ ገለጹ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የአራቱን ቋሚ ኮሚቴ የ2019 በጀት ዓመት የተቋማት 1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ በማካሄድ ላይ ይገኛል።
የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ካሰች ኤሊያስ በመክፈቻ ንግግራቸው እንዳሉት፤ አዲስና ነባር የምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ አባላት የመረጠን ህዝብ የጣለብንን ኃላፊነትና የሰጠንን አደራ እንዲሁም ከእኛ የሚጠብቀውን በቀጣይ 5 ዓመታት በብቃት መወጣት አለብን ብለዋል።
አዲስ የተመሠረተው የመደመር መንግስት ትኩረት ከህዝብ የተነሱ ጥያቄዎችን መመለስ መሆኑን ጠቁመው፤ በመንግስት የታቀዱ ብዙ ዕቅዶችን የማስፈፀም ኃላፊነት ቋሚ ኮሚቴው አለበት ነው ያሉት።
ወ/ሮ ካሰች ኤሊያስ አክለውም፤ የለውጡ መንግስት ከየትኛውም ጊዜ በላይ በህዝቡ ህይወት ላይ የሚታይ ለውጥ በቁጥር ብቻ ሳይሆን መሬት ላይ ማውረድ ትኩረት ማድረጉንም ገልጸዋል።
ከህግ አወጣጥ እስከ ክትትል ያሉ ተግባራት በምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎች በጥብቅ ዲስፒሊን መመራት ይኖርበታል ነው ያሉት ወ/ሮ ካሰች ኤሊያስ፡፡
በተለይም ከህዝቡ የሚነሱ የፍትሃዊነት ጥያቄዎችን እና የፍትሐዊ ተጠቃሚነት ምላሽ ለመስጠት ቋሚ ኮሚቴው በቁርጠኝነት መስራት ይጠበቅበታል ብለዋል።
የሚያጋጥሙ ችግሮችን በዕውቀትና በመግባባት በመፍታት በቀጣይ 5 ዓመታት ከህዝብ የተሰጠንን ኃላፊነታችንን መወጣት አለብን ብለዋል አፈ ጉባኤዋ።
ዘጋቢ፡ ፀሀይ ጎበና – ከአርባምንጭ ጣቢያችን

More Stories
የኩታ ገጠም የአስተራረስ ስርአትን በመጠቀም የግብርናውን ዘርፍ ማዘመንና ምርታማነትን ማሳደግ ወሳኝ መሆኑን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪና የግብርና ቢሮ ሀላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር ገለፁ
በኢትዮጵያ በሚቀጥሉት ዓመታት ለሚደረጉ የኢንዱስትሪ ሽግግሮች ግብርና መሠረት ነው ሲሉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የመንግስት ዋና ተጠሪና በብልጽግና ፓርቲ የክልሉ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ ተናገሩ
“የዘመነ ክህሎት ስነ ምህዳር ለዘላቂ ስራ እድል” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ ክልላዊ የንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ነው