ሀገራዊ ምክክሩ ኢትዮጵያ በዘመናት የመንግስት ታሪኳ ውስጥ የሚፈትናትን የሠላም ማጣት ሊቀርፍላት ይችላል ሲሉ በኣሪ ዞን የጂንካ ከተማ ነዋሪዎች ገለፁ

ሀገራዊ ምክክሩ ኢትዮጵያ በዘመናት የመንግስት ታሪኳ ውስጥ የሚፈትናትን የሠላም ማጣት ሊቀርፍላት ይችላል ሲሉ በኣሪ ዞን የጂንካ ከተማ ነዋሪዎች ገለፁ

‎አስተያየታቸውን ከሰጡን የጂንካ ከተማ ነዋሪዎች መካከል ሲስተር እታለም ሀብቴ፣ በየነ ገለቦና ሌሎችም እንደገለፁት፥ የሀገራችን መጻዒ ዕድል በጋራ ለመወሰንና በተለያዩ አለመግባባቶች እየተፈተነች ያለችን ይህችን ድንቅ ሀገር ሠላሟን ለማጽናት አዲስ ልምምድ መጀመሩ ጥሩ እርምጃ እና ችግሮቿን ሊቀርፍላት የሚችል መሆኑን ገልጸዋል።

‎ይህ ሀገራዊ ምክክር ሁሉም ኢትዮጵያዊ በጋራ ተሰማምቶ የሚኖርበትና የሚስራበት ሕብረ-ብሔራዊት ሀገር ከማስፈን አንጻር በመንግስታት መቀያየር ውስጥ የሚፀና ተቋም በመገንባት ረገድ ሚናው የላቀ እንደሚሆን አመላክተዋል።

‎በታሪክም በዚህ መልክ የመምከር ባህላችን ባለመዳበሩ ዛሬ ላለንበት ትርክት ዳርጎናል ያሉት አሰተያየት ሰጪዎቹ፥ የተነሱት አጀንዳዎችም የኢትዮጵያዊያን ያለመግባባት መንስኤ ሆነው መቆየታቸውን አንስተዋል።

‎በመሆኑም በዚህ መልክ የመምከር ልምምድ መጠናከሩና ሁሉንም ብሔር ብሔረሰብ በማሳተፍ በሃሳብ የበላይነት ለመተማመን መምከሩ አንዱ የዕድገት መገለጫ መሆኑን ገልጸዋል።

‎ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሀገር በትውልድ ቅብብሎሽ እንደምትቀጥል በማመን የሠላምና የእርቅ ባህላዊ ሥርዓቶቻችን ዘመን ተሻጋሪ ሆነው እንድቀጥሉ በመስራት ከራሳቸው ጀምሮ በጎ ማንነቶችን ለመገንባት እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

‎ዘጋቢ: ከተማ በየነ – ከጂንካ ጣቢያችን