የኩታ ገጠም የአስተራረስ ስርአትን በመጠቀም የግብርናውን ዘርፍ ማዘመንና ምርታማነትን ማሳደግ ወሳኝ መሆኑን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪና የግብርና ቢሮ ሀላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር ገለፁ
በመሬት አጠቃቀምና ተያያዥ የግብርና ልማት ስራዎች ላይ ትኩረት ያደረገ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በሀላባ ቁሊቶ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
እንደ ሀገር የምግብ ሉዓላዊነትን እውን ለማድረግ የተጀመረውን ጉዞ ለማፋጠን ልዩ ትኩረት ተሰቶ እየተሰራ ይገኛል።
በመድረኩ የተገኙት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪና የግብርና ቢሮ ሀላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር፤ ብልፅግናን በማህበረሰብ ደረጃ እውን ለማድረግና የምግብ ሉዓላዊነትን በዘላቂነት ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ዋነኛ መሰረት የሆነውን የመሬት ሀብት በተቀናጀ መልኩ መጠቀም አይነተኛ ሚና እንዳለው አስረድተዋል።
የሀገራችን ኢኮኖሚ ዋነኛ መሰረት የሆነው ግብርናን በማዘመንና የተሻሻሉ አሰራሮችን በመተግበር በዘርፉ የሚጠበቀውን ለውጥ ለማምጣት በቁርጠኝነት መስራት ያስፈልጋል ሲሉም አቶ ኡስማን በመድረኩ ጠቅሰዋል።
ምርታማነት ስንል መሬትን ብቻ አይደለም የሚሉት አቶ ኡስማን፤ የአምራቹን ጊዜና ጉልበት እንዲሁም የማምረቻ መሳሪዎችን ጭምር ያጠቃለለ እንደሆነም አመልክተዋል።
በመድረኩ ላይ ከፌደራል፣ ከክልል እና ከጂአይዜድ የተውጣጡ ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ዘጋቢ: ረዚቃ ተመስገን – ከሆሳዕና ጣቢያችን

More Stories
ምክር ቤቱ በህዝቡ ህይወት ላይ የሚታይ ለውጥ ለማምጣት እየሰራ እንደሚገኝ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ካሰች ኤሊያስ ገለጹ
በኢትዮጵያ በሚቀጥሉት ዓመታት ለሚደረጉ የኢንዱስትሪ ሽግግሮች ግብርና መሠረት ነው ሲሉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የመንግስት ዋና ተጠሪና በብልጽግና ፓርቲ የክልሉ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ ተናገሩ
“የዘመነ ክህሎት ስነ ምህዳር ለዘላቂ ስራ እድል” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ ክልላዊ የንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ነው