የጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ ደምስ ገብሬ አውደ ርዕዩን ባስጀመሩበት ወቅት እንደገለፁት፥ በዞኑ ከ790 በላይ የፈጠራ ስራዎች ውድድር በተማሪዎች፣ በኢንተርፕራይዞች እና በመምህራን እንዲሁም በኮሌጆች እና በግል ተሰርተው ቀርበዋል።
የፈጠራ ስራዎች ምዘናው ሲካሄድ በተገቢው በመከታተልና በአግባቡ በማስመዘን ለውጤት ማብቃት ይጠበቃል ሲሉም አሳስበዋል።
የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ ሀላፊ አቶ መብራቴ ወልደማሪያም በበኩላቸው የፈጠራ ስራዎች ውድድሩ በትክክለኛ መንገድ በመመዘን ውጤታማ ተወዳዳሪዎች በክልል መድረክ እንዲሳተፉ እድል የሚፈጥር ነው ሲሉም አስገንዝበዋል።
በዞኑ ካለፉት አራት አመታት ወዲህ በፈጠራ ስራዎች ውድድር አመርቂ ውጤት እየተመዘገበ እንደሆነ ያስታወሱት አቶ መብራቴ አሁንም ወቅቱ የሚፈልግውን የፈጠራ ስራ በመስራት እና በክልል ደረጃ ተፎካካሪ መሆን እንደሚገባም አመላክተዋል።
የፈጠራ ስራዎች ውድድሩ ለሁለት ተከታታይ ቀናት እንደሚቆይም ተመላክቷል።
ዘጋቢ፡ እርካብነሽ ወልደማርቆስ – ከወልቂጤ ጣቢያችን

More Stories
የኩታ ገጠም አስተራረስ ዘዴ እና የግብርና ቴክኖሎጂን በተገቢ መጠቀም ከጀመሩ ወዲህ ምርትና ምርታማነታቸው እያደገ መምጣቱን በከምባታ ዞን የዶዮገና ወረዳ አንዳንድ አርሶ አደሮች ተናገሩ
ብሔራዊ የዲጂታል ፋይዳ መታወቂያ መያዝ የተሻለ አገልግሎት ለማግኘት እንደሚጠቅም ተገለጸ
የዲጂታል ዘመን ኮሙኒኬሽን የመረጃ ስርጭት ብቻ ሳይሆን የሕዝብ እምነት የሚገነባበት እና የተቋማትን ገጽታ የሚያጠናክር መሆኑ ተገለጸ