በሚኒስትር ዴኤታ ኢንጂነር ሱልጣን ወሊ (ዶ/ር) የተመራል ኡክ በወላይታሶዶ ዩኒቨርሲ ቲየባዮ ጋዝ ማምረቻ ፕሮጀክትን የስራ እንቅስቃሴ ምልከታ አደረገ

በሚኒስትር ዴኤታ ኢንጂነር ሱልጣን ወሊ (ዶ/ር) የተመራል ኡክ በወላይታሶዶ ዩኒቨርሲ ቲየባዮ ጋዝ ማምረቻ ፕሮጀክትን የስራ እንቅስቃሴ ምልከታ አደረገ

ሀዋሳ፡ ሰኔ 12/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) በኢፌዲሪ ውሃና ኢነርጂሚኒስቴር የኢነርጂ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ በሆኑት ኢንጂነር ሱልጣን ወሊ (ዶ/ር) የተመራ ልኡክበ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ከአንድ አመት በፊት ተገንብቶ አገልግሎት እየሰጠ ያለየ ባዮ ጋዝማምረቻ ፕሮጀክትን የስራ እንቅስቃሴ ምልከታ አደረገ፡፡


እንደሃገር የመጀመሪያ የሆነውንና ከእንስሳት አዛባከ ኢነርጂ ባለፈ የተፈጥሮ ጋዝ እና ማዳበሪያን ማምረት የሚያስችለው ይኸው የባዮ ጋዝ ፕሮጀክት፤ከዚህ ቀደም የባዮ ጋዝ ምርት በተለይ በገጠሩ ማህበረሰብ ዘንድ በስፋት ለኢነርጂ አገልግሎት ብቻ ይውል ከነበረበት በውጭ ምንዛሬ የሚገባውን የአፈር ማዳበሪያ በተፈጥሯዊ መንገድ ከእንስሳት አዛባበሚገኝ ማዳበሪያ መቀየር የሚያስችል አዲስ ቴክኖሎጂን የሚተገብር ነው።


ልኡካን ቡድኑ ፕሮጀክቱ አሁንላይ ያለበትን ሁኔታ በተመለከተ ከዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንትና የማኔጅመንት አባላትጋር ሰፊ ውይይት አካሂደዋል።


ፕሮጀክቱ በአስራሶስት ወራት የትግበራ ሂደት ያሉበትን ክፍተቶች በተመለከተ ጥልቅ ውይይት የተካሄደ ሲሆንበ ዋናነት ፕሮጀክቱ ወደ ተግባር ሲቀየር ለዩኒቨርሲቲው የመብራት ሃይል አማራጭ በመሆን ለመማር ማስተማሩም ሆነ ምርምር ስራው አጋዥ እንዲሆን ማስቻል መሆኑን ነው በውይይቱ ወቅት የተነሳው።


ይሁን እንጂ የግብአት አቅርቦት በተፈለገው ልክ አለመሆን፣የግንዛቤ እጥረትና የመሳሪያው በሚፈለገው መጠን አለመስራት ተግዳሮት እንደሆነ ነው የተገለጸው።


በኢፌዲሪ ውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ኢንጂነር ሱልጣን ወሊ(ዶ/ር) በሃገሪቱ የመጀመሪያ የሆነውና ከባዮ ጋዝ የተፈጥሮ ነዳጅና ማዳበሪያን ማምረት እንዲችል በሚል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ከአለም አቀፍ ረጂ ተቋማት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ወደ ተግባር መግባቱን ገልጸዋል።


ፕሮጀክቱ አሁን ላይ ያሉበት ንክፍቶች በመለየት የታሰበውን አላማማሳካት እንዲቻል ሰፊ ውይይት ከዩኒቨርሲቲው የአመራር አካላትጋር ማድረጋቸውን ተናግረዋል።


ቴክኖሎጂው አዲስከ መሆኑጋር ተያይዞ በዘርፉ እውቀትያላቸው አካላትን በመጋበዝ በቀጣይ በተግባር የተደገፈ የአቅም ግንባታ ስልጠና ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እንደሚያዘጋጅም ጠቅሰዋል።


የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጉቼ ጉሌ(ዶ/ር) በበኩላቸው፤እንደሃገር አዲስ እና የመጀመሪያ የሆነው ይህን ፕሮጀክት ለምርምርም ሆነ ለማስተማሪያ ትልቅ መሳሪያ ሆኖ የሚያገለግል እንደ መሆኑ ለውጤታማነቱ የሁሉንም ርብርብ ይጠይቃል ብለዋል።


የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ፕሮጀክቱ አሁን ያለበትን ክፍተት በመድፈን ውጤታማ እንዲሆን እያደረ ገላለው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።


ዘጋቢ: ወንድወሰን ሽመልስ