በክልሉ በ2018 በጀት አመት ከ336 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ሀብት ከምዝበራና ከብክነት ማዳን መቻሉ ተገለጸ
ሀዋሳ፡ ሐምሌ 21/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) በክልሉ በ2018 በጀት አመት ከ336 ሚሊዮን 231 ሺ ብር በላይ የሚገመት ሀብት ከምዝበራና ከብክነት ማዳን መቻሉን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
ኮሚሽኑ የ2018 በጀት እቅድ አፈፃፀም ግምገማና የ2019 መሪ እቅድ ላይ የግብ ስምምነት ለማድረግ የተዘጋጀ የምክክር መድረክ በወልቂጤ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።
በመድረኩ ላይ የ2018 በጀት አመት የኮሚሽኑ አፈፃፀም ቀርቦ ግምገማ ነክ ውይይት እየተደረገ ይገኛል።
ከዚህ ባለፈ የ2019 በጀት ዓመት መሪ እቅድ ላይም የግብ ስምምነት የሚደረግ ስለመሆኑ ከመድረኩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
በክልሉ በ2018 በጀት አመት ከ336 ሚሊዮን 231 ሺ ብር በላይ የሚገመት ሀብት ከምዝበራና ከብክነት ማዳን መቻሉንም በቀረበው ሪፖርት ተገልጿል።
በምክክር መድረኩ ላይ የክልሉ ስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር አቶ ማሞ ቴጋን ጨምሮ ምክትል ኮሚሽነሮች፣ የተቋሙ ሠራተኞች፣ የክልል፣ የዞንና ልዩ ወረዳ የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ዳይሬክተሮችና ቡድን መሪዎች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።
ዘጋቢ፡ ሙባረክ አክመል – ከወልቂጤ ጣቢያችን

More Stories
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ማስፈፀሚያ ከ45.7 ቢሊየን ብር በላይ በጀት አፀደቀ
“አንድነት የሚገነባው በውይይት ነው፤ ሰላም የሚጠናከረው በመግባባት ነው” ኢማም ሐጂ አብዱልሃዲ ሼክ አህመድ ቡርሃን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት
መደበኛ ባልሆነ መልኩ የሎተሪ ዕድል ሙከራን “ዕቁብ” በሚል ሽፋን በህገ-ወጥ ተግባር ላይ የተሳተፉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ፍትህ ጽ/ቤት አሳሰበ