ሀዋሳ: ግንቦት 24/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ዛሬ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓመተ-ምህረት እየተካሄደ ይገኛል፡፡
በካፋ ዞን ከሚገኙ የምርጫ ክልሎች ውስጥ አንዱ በሆነው በቢጣ ጌሻ ምርጫ ክልል ዜጎች ሌሊት 11:30 ጀምረው ከቤታቸው በመውጣት በድምጽ መስጫ ጣቢያዎች ተገኝተዋል፡፡
ተንቀሳቅሰን የተመለከትናቸው የምርጫ ጣቢያዎች ላይ የተለያዩ የምርጫ ታዛቢዎች ተሟልተው መገኘታቸውን ማረጋገጥ ተችሏል፡፡
አስፈላጊ የፀጥታ አካላትም በምርጫ ጣቢያዎቹ የጽጥታ ሥራዎችን ለማገዝ በስፍራው ተገኝተዋል፡፡
በዚህም በየምርጫ ጣቢያዎቹ የተገኙ ዜጎች ይበጀናል ለሚሉት የፖለቲካ ፓርቲ ድምፃቸውን መስጠት ጀምረዋል፡፡
የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መልኩ የጀመረ ሲሆን የዜጎች ተሳትፎም ከወዲሁ ንቁ መሆኑን መገንዘብ ተችሏል፡፡
ዘጋቢ ፡ ዳንኤል መኩሪያ – ከቦንጋ ጣቢያችን

More Stories
ህዝበ ክርስቲያኑ የ2019 ዓ.ም የእንቁጣጣሽ በዓልን በሚያከብርበት ወቅት አቅመ ደካሞችን በመደገፍ ሊሆን እንደሚገባ የጠምባሮ ልዩ ወረዳ የሀይማኖት አባቶች ተናገሩ
የ2018 በጀት ዓመት ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ታላላቅ ስኬቶችን ያስመዘገበችበት እና የዲጂታል ሽግግር የሉዓላዊነቷ ምሰሶ መሆን የቻለችበት አመት መሆኑን አቶ አልማው ዘውዴ ገለፁ
ጳጕሜን 5 “የነገው ቀን” በኮሬ ዞን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው