ኢትዮጵያ በዛሬዉ ዕለት እያካሄደች የሚገኘውን 7ኛ ጠቅላላ ምርጫን ጨምሮ ሁሉንም ምርጫዎች መሳተፋቸውን የጃጁራ ከተማ አስተዳደር ነዋሪ የሆኑት፥ አቶ ዳንኤል ሌረሞ እና አቶ ዳየሞ ጡሜቦ ይገልፃሉ።
ነዋሪዎቹ እንደሚሉት፤ አንድ ድምፅ ለአሸናፊነት አልያም ለተሸናፊነት ሊያበቃ እንደሚችል ያላቸዉ ግንዛቤ በቀደሙት ምርጫዎችና በዘንድሮውም ጭምር እንዲሳተፉ አድርጓቸዋል።
ከእስከዛሬው ምርጫ በተለየ በርካቶች ወጥተዉ እየመረጡ መሆናቸው የዘንድሮዉ 7ኛ ጠቅላላ ምርጫ ለየት እንደሚያደርገውና በሰላምና ጤና ተገኝተዉ መሳተፍ በመቻላቸዉ የፈጠረባቸዉን ልዩ ስሜት ለደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ገልፀዋል።
በዚህም የመረጡት ፓርቲ አሸንፎ እንድትሆን የሚመኟት የወደፊቷን ኢትዮጵያ ለማስቀጠል የበኩላቸዉን ለመወጣት ስለዝግጁነትና ተስፋቸው ይናገራሉ።
የራስን እድል በራስ መወሰን ትልቅ አጋጣሚ መሆኑን ጠቁመዉ፤ ምርጫውን ነፃና ፍትሐዊ ሆኖ እንዳገኙትም አክለዋል።
ዘጋቢ ፡ ብዙነሽ ዘዉዱ

More Stories
ህዝበ ክርስቲያኑ የ2019 ዓ.ም የእንቁጣጣሽ በዓልን በሚያከብርበት ወቅት አቅመ ደካሞችን በመደገፍ ሊሆን እንደሚገባ የጠምባሮ ልዩ ወረዳ የሀይማኖት አባቶች ተናገሩ
የ2018 በጀት ዓመት ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ታላላቅ ስኬቶችን ያስመዘገበችበት እና የዲጂታል ሽግግር የሉዓላዊነቷ ምሰሶ መሆን የቻለችበት አመት መሆኑን አቶ አልማው ዘውዴ ገለፁ
ጳጕሜን 5 “የነገው ቀን” በኮሬ ዞን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው