በመሎ ኮዛ ምርጫ ክልል በላሃ ከተማ በላሃ ከተማ ቦክሬ ማዞሪያ ምርጫ ጣቢያ የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱን እንደ ተመላከተው ከማለዳ 12:00 ሰዓት የምርጫ አስፈፃሚዎችና ወኪል ታዛቢዎች በተገኙበት የድምፅ መስጫ ሳጥን ባዶ መሆኑና ሌሎች ቁሳቁሶች መሟላታቸው ተረጋግጦ የድምፅ መስጠት መርሀ-ግብሩ በይፋ ተጀምሯል።
የመራጭነት ካርድ የወሰዱ ዜጎች ከሌሊቱ 12፡00 ሰዓት አስቀድሞ ሰልፍ በመያዝ ድምጽ እየሰጡ ይገኛል፡፡
በቀዳሚነት ድምፅ ከሰጡት የመሎ ኮዛ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙሉነህ አውሳተው ከምርጫ በኋላ በሰጡት ሀሳብ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የዲሞክራሲ ስርዓትን መሰረት የምናስይዝበት ነው ብለዋል።
በወረዳው የብልጽግና፣ ኢዜማ ፣ ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት፣ነፃነትና ዕኩልነት፣ ኅብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ እና የኢትዮጵያ ዴሞክራቲክ ኅብር ፓርቲዎች ይፎካከራሉ።
ዘጋቢ፡ ድጋፌ ድክሬ – ከሳውላ ጣቢያችን
በመሎ ኮዛ ምርጫ ክልል በሁሉም ምርጫ ጣቢያዎች 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ድምፅ መስጠት ተጀመረ

More Stories
በክልሉ በ2018 በጀት አመት ከ336 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ሀብት ከምዝበራና ከብክነት ማዳን መቻሉ ተገለጸ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ማስፈፀሚያ ከ45.7 ቢሊየን ብር በላይ በጀት አፀደቀ
“አንድነት የሚገነባው በውይይት ነው፤ ሰላም የሚጠናከረው በመግባባት ነው” ኢማም ሐጂ አብዱልሃዲ ሼክ አህመድ ቡርሃን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት