ከ107 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ18 ነጥብ 7 ኪ.ሜ አዲስ የመንገድ ግንባታ ተጀመረ
ሀዋሳ፡ ግንቦት 18/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) በየደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትራንስፖርትና መንገድ ልማት አስተዳደር ቢሮ በጎፋ ዞን መሎኮዛ ወረዳ ከ107 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ18 ነጥብ 7 ኪ.ሜ አዲስ የመንገድ ግንባታ አስጀመረ።
በጎፋ ዞን መሎኮዛ ወረዳ የሚስተዋለውን የመንገድ ጥያቄ ለመመለስ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተመላክቷል።
የመሎ ኮዛ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙሉነህ አውሳቶ ህብረተሰቡ የረዥም ዘመናት ጥያቄ ሆኖ የቆየው የመንገድ ግንባታ ሥራው በተቆረጠለት ጊዜ በፈጥነት ተጠናቆ ለሕዝብ አገልግሎት እንዲደርስ እንዲደርግ ጥሪ አቅርበዋል።
የጎፋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና ስራና ክህሎት መምሪያ ኃላፊ አቶ ምናሴ ኤሊያስ፤ የመንገዱ መጀመር በወረዳው ምርትና ምርታማነትን በመጨመር የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት በማረጋገጥና የገበያ ትሰሰር እንደሚያሳልጥ ተናግረዋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትራንስፖርትና መንገድ ልማት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ ተወልደ ተሰፋዬ የመንገዱ ስራ በገጠር ትስስርና በምግብ ዋስትና ፕሮግራም አማካኝነት የሚሰራ መሆኑ ተናግረዋል።
በ107 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር 18.7 ኪ.ሜ የሚሰራው ከወረዳ ከዞን እስከ ክልል ያሉ የመንግስት ተቋማት በማቺንግ ፈንድ የሚተገበር ሲሆን 70% በአለም ባንክ ድጋፍ የሚሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
የመንገዱ ስራ በቀጣይ አራት ወራት የሚጠናቀቅ ሲሆን ከወረዳ እስከ ክልል ያሉ የመንግስት አካላት ድጋፍና የቅርብ ክትትል የሚደረግ መሆኑን ጠቁመዋል።
ዘጋቢ፡ ስንታየሁ ሙላቱ – ከሳውላ ጣቢያችን

More Stories
የብራይት ፕሮጀክት የሴቶችንና ህፃናትን የስራ ጫና ከማቃለል ባሻገር የንፁህ መጠጥ ውሀ ተደራሽነት ላይ የሚመታይ ተግባር ማከናወኑን የጋሞ ዞን ውሀና ኢነርጂ መምሪያ አስታወቀ
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ጥናታቸው በተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች ላይ ያተኮረ የማረጋገጫ ወርክሾፕ እና የርክክብ መርሃ ግብር እያካሄደ ይገኛል
የማህበረሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመፍታት የቤት ልማት አቅርቦት ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ