ማንቸስተር ዩናይትድ አንድሬ ሳንቶስን አስፈረመ
ማንቸስተር ዩናይትድ አንድሬ ሳንቶስን ከቼልሲ በይፋ አስፈርሟል።
ማንችስተር ዩናይትድ ተጫዋቹን በ50 ሚልዮን ፓውንድ ሲያስፈርም ቼልሲ ከወደፊት ሽያጩ 10 በመቶ ድርሻ የሚያገኝ ይሆናል።
በዚህ ክረምት ለቀያይ ሰይጣኖች የመጀሪያው ፈራሚ የሆነው የ22 ዓመቱ አንድሬ ሳንቶስ ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር ተጨማሪ 12 ወራትን ያካተተ የ5 ዓመት ኮንትራት መፈራረሙ ተገልጿል።
በዝውውር መስኮቱ በዋነኝነት የአማካይ ክፍሉን ለማጠናከር እንቅሰቃሴ በማድረግ ላይ የሚገኘው ማንቸስተር ዩናይትድ ቤልጂዬማዊውን አማካይ ዩሪ ቴሊማንስን ከአስቶንቪላ ለማስፈረም ከስምምነት ላይ መድረሱ ታውቋል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
“ኤርሊንግ ሀላንድን አምበል የምናደርገዉ ከሆነ ትልቅ ችግር ዉስጥ እንገባለን” ኤንዞ ማሬስካ
ክርስቲያኖ ሮናልዶ እና ጆርጂና ሮድሪጌዝ የጋብቻ ስነ ስርዓታቸውን ፈፀሙ
ሶማሊያዊው ዳኛ ኦማር አርታን የዩኤፋ ሱፐር ካፕን በዋና ዳኝነት በመምራት የመጀመሪያው አፍሪካዊ ሊሆኑ ነው