ሀዋሳ፡ ሐምሌ 07/2018 ዓ.ም(ደሬቴድ) “ወሰን ተሻጋሪ በጎ አድራጎት ማህበር” አባላት በጎፋ ዞን ለሦስት ተከታታይ ቀናት በመቆየት በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ የበጎ ፈቃድ ሥራዎችን እንደሚያከናውኑ ገለጹ።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ማርቆስ ማቴዎስ፣ ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ወጣቶች የሀገራቸውን ብዝሃነት እንዲያውቁ፣ አንድነታቸውን እንዲያጠናክሩ እና ለተሻለ ኢትዮጵያ ግንባታ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ተናግረዋል።
የማህበሩ አስተባባሪ ወይዘሮ የሺሐረግ ተፈሪ በበኩላቸው “ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ቃል ለአምስተኛ ዙር የሚካሄደው መርሃ ግብር የወጣቶችን ግንኙነት በማጠናከር እና የማህበረሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች በመቅረፍ ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ ገልጸዋል።
የጎፋ ዞን የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ጋሻያለው ገላ በበኩላቸው፣ ወሰን ተሻጋሪ የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት የኢትዮጵያን እድገት ለማፋጠን እና ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስሮችን ለማጠናከር ጉልህ ሚና እንዳለው ገልጸው፣ በጎ ተግባር ዘር፣ ሃይማኖትና ጎሳን የማይለይ መሆኑን አስታውቀዋል።
የማህበሩ አባላትም በጎፋ ዞን በሚያደርጉት የሦስት ቀናት ቆይታ የተለያዩ መልካም ተሞክሮዎችን እንደሚለዋወጡ ገልጸዋል።
ዘጋቢ፡ ስንታየሁ ሙላቱ – ከሳውላ ጣቢያችን

More Stories
በክልሉ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠል አለባቸዉ – ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ
የሕዝባችንን የልማት ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ የመመለስና ሜጋ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት የማጠናቀቅ ቁርጠኝነታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
ሞዴል የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን መሠረተ ልማት ማሟላትና ምቹ የመማሪያ ከባቢን ለልጆች መፍጠር ለቀጣዩ የትምህርት ደረጃዎች መሠረት መሆኑ ተገለጸ