ከ21 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የተገነባው የጂንካ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት የተጠርጣሪ ማቆያና የቢሮ ህንጻ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ አለማየሁ ባውዲ እና የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍስሃ ጋረደው በተገኙበት በደማቅ ሥነ ስርዓት በይፋ ተመረቀ
በማህበረሰብ ተሳትፎ በተገነባው ህንጻ ምረቃ ላይ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና ከፍተኛ የጸጥታ ዘርፍ አመራሮች ተገኝተዋል።
በህዝብ ተሳትፎ የተገነባው የጂንካ ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት ለዓመታት ሲያገለግል የቆየውን የፖሊስ ተቋም በአዲስ መልክ መቀየር ያስችላል ተብሏል።
ከ21 ሚሉዮን ብር በላይ ወጭ የተገነባው ህንጻ በልዩ የባዛር ዝግጅት በድምቀት የመረቁት የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ አለማየሁ ባውዲ እና የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍስሃ ጋረደው በጋራ በመሆን ነው።
በሥነ ሥርዓቱ ላይ የክልሉ ከፍተኛ የጸጥታ አመራሮች በልዩ የባዛር ዝግጅት ላይ በክብር እንግድነት ታድመዋል።
ለ3 ቀናት በሚቀጥለው የባዛር ዝግጅት ከ12 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ለማግኘት የታቀደ ሲሆን ይህም የተቋሙን የውስጥ ግብዓት ለማሟላት በማለም የተሰናዳ መሆኑን ከአስመራቂ ኮሚቴ አመራሮች መረዳት ተችሏል።
ዘጋቢ፡ ወንድሜነህ አድማሱ – ከጂንካ ጣቢያችን

More Stories
የአርብቶ አደሩን ማህበረሰብ በመንገድ መሠረተ ልማት ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መሰኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ አሰታወቀ
ሳውላ ከተማን ለኢንቨስትመንትና ለቱሪዝም ምቹ የማድረግ የ5 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት ሥራ እየተካሄደ ነው
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የቱሪዝም ሀብቶችን በማልማትና ሰላምን በማጽናት ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የማድረግ ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል